ሽታይንብሩክ የ ኤስ ፕዴ እጬ ተወዳዳሪ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 01.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ሽታይንብሩክ የ ኤስ ፕዴ እጬ ተወዳዳሪ

SPD በታህሳስ ወር በሚያካሂደው ጉባኤ በእጩ ተወዳዳሪነነት በይፋ የሚሰየሙት የ65 አመቱ ሽታይንብሩክ በመጪው ምርጫ ከክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲዋ አንጌላ ሜርክላ ጋር ነው የሚፎካከሩት ። ሽታይንብሩክ ከምርጫው በኋላ እንደተናገሩት በምርጫ ዘመቻ ወቅት የሚያተኩሩት በሜርክል የዩሮ ቀውስ አያያዝ ላይ ነው ።


የጀርመን ሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ በጀርመንኛው ምህፃር SPD የቀድሞውን የገንዘብ ሚኒስትር ፔር ሽታይንብሩክን  በመጪው አመት ለሚካሄደው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ አድርጎ መምረጡን ዛሬ አስታውቋል ። SPD በታህሳስ ወር በሚያካሂደው ጉባኤ  በእጩ ተወዳዳሪነነት በይፋ የሚሰየሙት የ65 አመቱ ሽታይንብሩክ በመጪው ምርጫ ከክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲዋ አንጌላ ሜርክላ ጋር ነው የሚፎካከሩት   ። ሽታይንብሩክ ከምርጫው በኋላ እንደተናገሩት በምርጫ ዘመቻ ወቅት የሚያተኩሩት በሜርክል የዩሮ ቀውስ አያያዝ ላይ  ነው ። ስለ ሽታይንብሩክ ማንነትና በእጩ ተወዳዳሪነት እንዴት ሊመረጡ እንደበቁ የበርሊኑን ዘጋቢያችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ ጠይቄዋለሁ ።
ይልማ ኃይለ ሚካኢል
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ  

Audios and videos on the topic