ሽልማት ለቀድሞዉ የፖለቲካ እስረኛ | ኢትዮጵያ | DW | 17.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሽልማት ለቀድሞዉ የፖለቲካ እስረኛ

ቤልጂየምና ሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ማኅበራት አቶ አበራ የማነአብ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ዉስጥ ላደረጉት አስተዋጽኦ ሽልማት ሰጥተዋል።

ሽልማቱ በሁለቱ ሃገራት የሚኖሩ ወገኖችን ባለፈዉ ወር መጨረሻ አምስተርዳም ከተማ ላይ ባሰባሰበዉ ሕዝባዊ ስብሰባ ወቅት የተሰጠ ሲሆን፤ አቶ አበራ በፖለቲካዉ ሂደት ለከፈሉት መስዋዕትነትና ላሳዩት ጽናት የአክብሮትና ምስጋና መግለጫ እንደሆነም ተገልጿል። አቶ አበራ የማነአብ በ1986ዓ,ም መንግስት በጠራዉ የእርቅና ሰላም ጉባኤ ለመሳተፍ ወደአዲስ አበባ በሄዱበት ወቅት ተይዘዉ ለ17 ዓመታት ታስረዉ መቆየታቸዉ ይታወሳል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ አቶ አበራን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic