ሻኪሶ ከሥራ ማቆም እስከ አደባባይ ተቃውሞ | ኢትዮጵያ | DW | 08.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሻኪሶ ከሥራ ማቆም እስከ አደባባይ ተቃውሞ

በሻኪሶ የወርቅ ማዕድን ማውጫ እና በአቅራቢያው በሚገኘው ክብረ-መንግሥት ከተማ ነዋሪዎች፦ ከወርቅ ማዕድን ማምረቻው የሚወጣው ዝቃጭ ለጤናችን ችግር ፈጥሮብናል ሲሉ ለሦስት ቀናት የሥራ እንቅስቃሴ አቁመዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:55

የሻኪሶ እና አካባቢው ነዋሪዎች ሥራ ማቆም

በሻኪሶ የወርቅ ማዕድን ማውጫ እና በአቅራቢያው በሚገኘው ክብረ-መንግሥት ከተማ ነዋሪዎች፦ ከወርቅ ማዕድን ማምረቻው የሚወጣው ዝቃጭ ለጤናችን ችግር ፈጥሮብናል ሲሉ ለሦስት ቀናት የሥራ እንቅስቃሴ አቁመዋል። በአካባቢው ከትናንት ጀምሮ በሥራ ማቆም የጀመረው ተቃውሞ ዛሬ ወደ ግጭት መቀየሩን እና አስለቃሽ ጢስ መተኮሱን ሁለት ሰዎችም በከባድ ኹኔታ መቁሰላቸውን ፓርቲያቸው በአካባቢው ተጠሪ እንዳለው የገለጡት የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። ሌላ የአካባቢው ነዋሪን እና የሻኪሶ ከንቲባን በማነጋገር ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ከአዲስ አበባ ልኮልናል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic