ሻርለት ማቄኬ - ፋናወጊዋ ደቡብ አፍሪካዊት ታጋይ | ራድዮ | DW | 28.06.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ራድዮ

ሻርለት ማቄኬ - ፋናወጊዋ ደቡብ አፍሪካዊት ታጋይ

ደቡብ አፍሪካውያን የሀገራቸውን ልጅ ሻርለት ማኒያ ማቄኬን “በገነት ያለ መልዐክ ያለውን ድምጽ አድሏቸዋል” ይሏቸዋል። በእርግጥም መዝፈን የማቄኬ ህይወት መሆኑ ነበር። ዓለምን የመዞር ዕድል ያጋጠመውን የዝማሬ ቡድን (ኳየር) ከተቀላቀሉ በኋላ ግን ያልተጠበቀ ዕጣ ፈንታ የህይወታቸውን አካሄድ ቀየረው። ያ አጋጣሚ ማቄኬን “የጥቁሮች የነጻነት እናት” የሚል ስያሜ ወዳሰጣቸው ትግል መርቶታል። የማቄኬ አስደናቂ ስኬቶች በታሪክ መጽሐፍት ለረጅም ጊዜ ገሸሽ ተደርገው ቆይተዋል። ነገር ግን በደቡብ አፍሪካ እኩል መብት ለማግኘት በተደረገው ትግል ዋና ሚና መጫወታቸው አሁን እውቅና አግኝቷል። #ARAMH

ቪድዮውን ይመልከቱ። 01:48