ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ 10ኛ ዓመቱን አከበረ   | ባህል | DW | 25.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ 10ኛ ዓመቱን አከበረ  

ለየት ባለ አቀራረቡ ተደማጭነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ የሚነገርለት የራድዮ ጣቢያው መሥራች እና ባለቤት ወይዘሮ መዓዛ ብሩ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የስኬታቸው ሚስጥር አማራጭ ሆነው መቅረብ መቻላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:19
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:19 ደቂቃ

ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ 10ኛ ዓመት


ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ የተመሠረተበትን አሥረኛ ዓመት ትናንት በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት በሸራተን አዲስ አክብሯል። ለየት ባለ አቀራረቡ ተደማጭነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ የሚነገርለት የራድዮ ጣቢያው መሥራች እና ባለቤት ወይዘሮ መዓዛ ብሩ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የስኬታቸው ሚስጥር አማራጭ ሆነው መቅረብ መቻላቸው መሆኑን ገልፀዋል። ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ ቀለል ባለ አቀራረብ እያዝናኑ በሚያስተምሩ ዝግጅቶቹ ይበልጥ ሳቢ መሆን መቻሉን አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ 

Audios and videos on the topic