ሶስት ሚኒስትሮች ተሾሙ  | ኢትዮጵያ | DW | 18.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሶስት ሚኒስትሮች ተሾሙ 

ምክር ቤቱ ዛሬ  አቶ ለማ መገርሳን የመከላከያ ሚኒስትር ፡ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ወይዘሮ አይሻ ሙሃመድን የከተማ ልማትና  ኮንስትራክሽ ሚኒስትር አድርጎ በአብላጫ ድምጽ ሾሟል፡።በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድም አልተገኙም። ምክንያቱም አልተገለጸም።

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የሶስት ሚኒስትሮችን ሹመት አጽድቋል። ምክር ቤቱ ዛሬ  አቶ ለማ መገርሳን የመከላከያ ሚኒስትር ፡ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ወይዘሮ አይሻ ሙሃመድን የከተማ ልማትና  ኮንስትራክሽ ሚኒስትር አድርጎ በአብላጫ ድምጽ ሾሟል፡፡  ሦስቱ ሰዎች የተሾሙት በክልል ተመዝግቦ የነበረውን ጠንካራ የለውጥ ሂደት ሃገራዊ አድርጎ ለማስቀጠል ፣የህግ የበላይነትን እና የፌደራል ስርዓቱን ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል። ተሿሚዎቹ  አቶ ለማ መገርሳ እና ወይዘሮ አይሻ መሃመድ በምክር ቤቱ ተገኝተው ቃል መሀላ ሲፈጽሙ አቶ አንግዳርጋቸው ገዱ ግን አልተገኙም። ያልተገኙበት ምክንያትም አልተነገረም ።በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድም አልተገኙም። ምክንያቱም አለመገለጹን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዘግቧል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ