ሶርያ፤ የተኩስ አቁም ስምምነት | ዓለም | DW | 27.02.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሶርያ፤ የተኩስ አቁም ስምምነት

ሶርያ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በአብዛኛው የሶርያ አካባቢ ጸጥታ እንደሰፈነ ተገለፀ።

ኾኖም መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው የሶርያ የሰብዓዊ መብት ታዛቢ ቡድን ራሱን «እስላማዊ መንግሥት» እያለ የሚጠራው ቡድን ብርቱ ውጊያ መክፈቱን ጠቅሷል። በውጊያው ቢያንስ 45 የ IS ተፋላሚዎች እና 20 የኩርድ ተዋጊዎች እንዲሁም የፀጥታ ኃይላት ዛሬ መገደላቸውንም ቡድኑ አክሎ ገልጿል።

ምንም እንኳን የሩሲያ የጦር አይሮፕላኖች ዓርብ ዕለት በሶርያ የመንግሥት ተቃዋሚ አማፂያን ላይ ጠንካራ የኃይል ርምጃ የወሰዱ የነበረ ቢሆንም ዛሬ አይሮፕላኖቹ በሰማይ ላይ አልተስተዋሉም። ዩናይትድ ስቴትስ እና ሩሲያ በሳምንቱ መጀመሪያ ነበር ለተኩስ አቁም የተስማሙት። ይህ ስምምነት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሰው እና ራሱን እስላማዊ ቡድን ሲል የሚጠራውን የሽብር ቡድን እና የአል ኑርሳ ግንባር ቡድንን አያካትትም። ተኩስ አቁሙ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በጥቂት አካባቢዎች ብቻ የተኩስ ልውውጥ እና ውጊያ ተስተውሏል።

ልደት አበበ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተዛማጅ ዘገባዎች