ሶሪያ፥ የሩሲያና የዩናይትድ ስቴትስ ዕቅድ | ዓለም | DW | 08.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሶሪያ፥ የሩሲያና የዩናይትድ ስቴትስ ዕቅድ

የፖለቲካ አዋቂዎች እንደሚሉት የኬሪ የመጀመሪያ አላማ ባይሳካም ከሞስኮ ባለሥልጣናት ጋር የደረሱበት ሥምምነት አስጊዉን የሶሪያ የርስ በርስ ጦርነት ለማቀላል መርዳቱ አይቀርም።

Russia's Foreign Minister Sergei Lavrov (R) and U.S. Secretary of State John Kerry talk during their meeting in Moscow, May 7, 2013. Russia and the United States agreed on Tuesday to try to arrange an international conference this month on ending the civil war in Syria, and said both sides in the conflict should take part. REUTERS/Mladen Antonov/Pool (RUSSIA - Tags: POLITICS CONFLICT)

ኬሪና ላቭሮቭ


የሶሪያ ተፋላሚ ሐይላት የሚደራደሩበትን ሥልት የሚቀይስ ዓለም አቀፍ ጉባኤ እንዲደረግ የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ ባለሥልጣናት ተስማሙ።የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ሞሶኮ ዉስጥ ከሩሲያ መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በሕዋላ የወጣዉ የሁለቱ መንግሥታት የጋራ መግለጫ እንዳመለከተዉ ጉባኤዉ ምናልባት በሚቀጥሉት ሰወስት ሳምንታት ዉስጥ ይደረጋል። የአሜሪካዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ሞስኮ የተጓዙት ሩሲያ ለሶሪያ መንግሥት የምትሰጠዉን ድጋፍ እንድታቋርጥ ወይም እንድትቀንስ ለማግባባት ነበር።የፖለቲካ አዋቂዎች እንደሚሉት የኬሪ የመጀመሪያ አላማ ባይሳካም ከሞስኮ ባለሥልጣናት ጋር የደረሱበት ሥምምነት አስጊዉን የሶሪያ የርስ በርስ ጦርነት ለማቀላል መርዳቱ አይቀርም።በዚሕ ጉዳይ ላይ ከበርሊኑ ወኪላችንን ከይልማ ሐይለ ሚካኤል ጋር አጭር የስልክ ዉይይት አድርገናል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic