ሶሪያውያን ስደተኞች በቱርክ | ዓለም | DW | 09.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሶሪያውያን ስደተኞች በቱርክ

በሶሪያ መንግሥት ወታደሮችና በተቃዋሚዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ሰበብ ቱርክ ፣ ከሊባኖስ ቀጥሎ የሶሪያ ስደተኞች መጉረፊያ ሆናለች ።

default

የሶሪያ ሰደተኞች ወደ ቱርክ ሲያቀኑ

በተለይ ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ ከተማ ውስጥ 120 ያህል የመንግሥት ወታደሮች ከተገደሉ ወዲህ ወደ ቱርክ የሚሸሹት የሶሪያ ስደተኞች ቁጥር ጨምራል ። በወታደሮቹ ግድያ ምክንያት የሶሪያ ልዩ ኮማንዶ በከተማይቱ ላይ የተጠናከረ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል የሚል ስጋትም ሰፍኗል ። በአሁኑ ሰዓት በርካታ የሶሪያ ስደተኞች ወደ ቱርክ መጉረፋቸውም ቱርክ ስለ ሶሪያ መንግሥት ያላትን አቋም ሊያስቀይር ይችል ይሆናል የሚል ግምት አሳድሯል ። ኡልሪሽ ፒክ ከኢስታንቡል ለላከው ዘገባ ሂሩት መለሰ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic