ሶሪያና የውክልናው ጦርነት፣ | ዓለም | DW | 30.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሶሪያና የውክልናው ጦርነት፣

በሶሪያ ተደራራቢ ውዝግቦች ናቸው የተከሰቱት። በፈላጭ ቆራጩ አገዛዝና በተቃውሞው ወገን መካከል ፣ የእርስ በርሱ ጦርነት ከተጀመረ ከ ሁለት ዓመት በላይ ሆኗል። ሌሎች በተለያዩ ምክንያቶች ጣልቃ መግባት ከጀመሩም ከራርሟል። ጣልቃ የገቡት ክፍሎች፤

ጦርነቱ አካባቢያዊ መልክ እንዲያዝና ዓለም አቀፍ ተጽእኖም እንዲያጅበው በማድረግ ላይ ናቸው። ከምዕራባውያን ሃገራት ፤ ሩሲያና ቱርክ ሌላ፤ በተለይ ኢራን ፤ ስዑዲ ዐረቢያና ቐጠር ሶሪያ ውስጥ በትንንቅ ላይ ያሉ ነው የሚመስሉት። ሦስቱ መንግሥታት ፤ ሶሪያ ውስጥ የቅክልና ጦርነት ነው በማካኼድ ላይ የሚገኙት። ይህን የሚያደርጉትም ፤ በዚያ አካባቢ የተሰሚነቱን ዕድል ለማግኘትም ሆነ የመሪነቱን ቦታ ለመያዝ ነው።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic