ሶማልያ እና የመንግሥት ምስረታ ሂደት | አፍሪቃ | DW | 16.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ሶማልያ እና የመንግሥት ምስረታ ሂደት

ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ መንግሥት አልባ ሆና የቆየችዉ ሶማልያ፤ ዓለም አቀፍ እዉቅና ያለዉ መንግሥት ከመሰረተች ገና ሁለት ዓመትዋ ነዉ።

ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ ለሚመራዉ የሶማልያ መንግሥት እዉቅና ብቻ ሳይሆን ሙሉ ድጋፍም በመስጠት በሶማልያ ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዲሰፍንና መንግስቱ ተጠናክሮ የሀገሪቱን አንድነትና ሰላም እንዲያስጠብቅ ለማድረግ የበኩሉን እያደረገ ነዉ። 22 ሺህ የሚሆኑ የሰላም አስከባሬ ጓዶች በሶማልያ ግዳጅ ላይ ሲሆኑ፤ ከሰማልያ የወታደሮች ጋር በመሆን በአሸባብ ላይ ባደረጉት ጥቃት በርካታ አካባቢዎችና ከተሞችን ነፃ እንዳወጡ ታዉቋል። ይሁን እንጂ፣ አሁንም አሸባብ ጥቃት የማድረስ አቅም እንዳለዉ ይታመናል። አሸባብ ከዓለም ዓቀፍ የአሸባሪ ቡድኖች ጋር ካለዉ ግንኙነት እና በአስራጨዉ የአክራሪነት አስተምሮ በአጭር ጊዜ ከአካባቢዉ ማስወገድ አስቸጋሪ እንደሚሆን ግልፅ ነዉ። የሶማልያ መንግሥትም ቢሆን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያሳትፍ መንግሥታዊ መዋቅር በመመስረት በኩል ገና ብዙ እንዳልተጓዘ እና ብዙ ችግሮች እንዳሉበት የሚነገር ሲሆን፤ ጋዜጠኞችን በማዋከብ እና በማሰርም ይወቀሳል። አንዳንድ በግዳጅ ላይ የሚገኙ የአፍሪቃ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ኃይላትም እርዳታ የሚሹ የሶማልያ ሴቶችን የሚደፍሩ መሆኑን የሚያጋላጥ ዘገባ ይፋ ሆንዋል። በሶማልያ ስላለዉ የመንግሥት ግንባታና ችግሮቹ፤ በብራስልስ የሚገኘዉ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ፤ በሶማልያ የመንግሥታቱ ድርጅት ተወካይ ኔኮላ ኬይን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic