ሶማልያና የመሪዎችዋ ውዝግብ፤ | አፍሪቃ | DW | 29.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ሶማልያና የመሪዎችዋ ውዝግብ፤

የሶማልያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሙሐመድ ጠ/ሚንስትር አብዲ ፋራህ ሺርዶን ሥልጣን እንዲለቁ በመጠየቃቸው ገና በሁለት እግሮችዋ መቆም ያልቻለችውን ሀገር ለሌላ ዙር ቀውስ እንዳይዳርጋት አሥጋቷል። የሁለቱ መሪዎች አለመጣጣም ሰበብ ምን እንደሆነ በትክክል

ለማወቅ አልተቻለም። ፖለቲከኞች ግን፤ ሙስና፤ የግል ታማኝነት ጥያቄ፤ እንዲሁም የተወሳሰበው የጎሣ ፖለቲካ ስሜት ሳይሆን እንዳልቀረ ነው የጠቁሙት። የአፍሪቃ ኅብረትና የ ተ መ ድ ትኩረት ስላደረጉበት ሀገር ወቅታዊ ውዝግብ ፣ ተክሌ የኋላ በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙትን የጸጥታ ጥናት ተቋም ባልደረባ አንድርውስ አታ አሳሞዋን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

በጥር ወር 1982 ዓ ም ፤ የቀድሞው አምባገነን ሲያድ ባሬ ከሥልጣን ከተወገዱ ወዲህ፤ በጎሳ ጦር አበጋዞች ፍልሚያ የተደላደለ ማዕከላዊ መንግሥት መመሥረት ተስኗት በቀውስ የቆየችው ሶማልያ፣ በአፍሪቃ ኅብረትና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ መንግሥት እንድትመሠርት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው። በሀገሪቱ ደቡባዊውና ማዕከላዊው ግዛት በተወሰነ ቦታ ተጠናክሮ የሚገኘው ከአል ቃኢዳ ጋር ቁርኝት እንዳለው የሚነገርለት እክራሪው እስላማዊ ድርጅት አሸባብ በበኩሉ ያሁኑን የሽግግር መንግሥት አሽቀንጥሮ ለማጣል ነው የሚያደባው። በሶማልያ አመኔታ የሚጣልበት መንግሥት ለመመሥረት ካልተቻለ ፤አሸባብን ፈጽሞ ማዳከምም ሆነ ማጥፋት የሚቻል አይሆንም።

ሶማልያን አሁን በአመራር ደረጃ እንዴት አነታራኪ ሁኔታ ሊያጋጥማት ቻለ?

በደቡብ አፍሪቃ የጸጥታ ጥናት ተቋም ባልደረባ አንድርውስ አታ አሳሞዋ---

«በመጀመሪያ ፤ እንደሚመስለኝ፤ በቅርቡ የሶማላያ ታሪክ እንዲህ ዓይነቱን ለመታዘብ መብቃት አዲስ ነገር አይደለም። ቀደም ያለውን የሽግግር መስተዳድር አወቃቀርና አሠራር ብታስታውስ፣ የአሁኑን መንግሥት ለመመሥረትም በተካሄደው ውጣ-ውረድ የነበረው ውስጣዊ ክፍፍል፣ በጠ/ሚንስትሩና በፕሬዚዳንቱ መካከል ቀላል አልነበረም። በሽግግሩ ወቅት በየጊዜው ያጋጠመና ሂደቱንም ያዳከመ ጉዳይ ቢኖር ይኸው በፕሬዚዳንትና በጠ/ሚንስትር መካከል ያለ የሥልጣን ክፍፍል ነው። አሁን የሚያሳስበው ውስጣዊው ክፍፍል ከሞላ ጎደል የሚያንጸባርቀው የመስተዳድር መዋቅር ደካማነት ነው። ይህ መስተዳድር ወይም መንግሥት ደግሞ በሰፊው ተስፋ የተጣለበት እንደነበረ አይታበልም።

ማንኛውም የደካማነት ነጽብራቅ ፣ አሸባብ ምንጊዜም ይህን መንግሥት በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የተቋቋመ እንጂ በራሱ እግር የማያቆም ነው በማለት ለሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ዋጋ መስጠት እንዳይሆን ጥንቃቄ ያሻል። ሶማልያ እንደተባለው በጎሳ፤ በአምቻ-ጋብቻና ዝምድናየተማከለ የአገዛዝ ስልት ከመከተል መላቀቅ የቻለች አገር አይደለችም።»

ከመጀመሪያው የሽግግር ወቅት መስተዳድር ድክመት በመነሳት አሁን ሥጋት ያደረበት ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለሥጋቱ በቂ ምክንያት አለ ማለት እንችላለን?

«የአፍሪቃ ሕብረት፤ በተለይም የ ተ መ ድ አሁን ሶማልያ የያዘችውን አቅጣጫ ፈር በማስያዝ ረገድ ተጽዕኖም ሆነ ግፊት ማድረግ የቻለ ነው። «አሚሶን» የከፈለው መስዋዕትነት መቅዲሹ ውስጥ የሚገኙ የ ተ መ ድ ተወካዮች ጭምር ግምት የሚሰጣቸው ናቸው። ስለዚህ እነዚህ ሁለት ወገኖች የተጣመመውን ለማቃናት ባፋጣኝ ቢገቡና የሚቻላቸውን ተግባር ቢፈጽሙ መልካም ነው። በመጀመሪያ ስለሁኔታው ግንዛቤ ቢጨብጡና የሕገ-መንግሥቱን ተጨባጭ ይዞታም ቢመረምሩ ማለፊያ ነው።»

የሶማላያ ጠ/ሚንስትር አብዲ ፋራህ ሺሪዶን ክርክሩ ሕገ-መንግሥትን የተመለከተ ነው ባይ ናቸው። ሕገ-መንግሥቱ እርግጥ ፕሬዚዳንቱ ጠ/ሚንስትሩን ይመርጣል ይላል። እንደገናም ጠ/ሚንስትሩ የሚንስትሮች ም/ቤት ሰብሳቢ ባለሥልጣንም ነው። ሕገ-መንግሥቱ፣ ፕሬዚዳንቱ ስላለው የመሻር ሥልጣን በግልጽ አላስቀመጠም። ይህ ምን ማለት ነው። ጠ/ሚንስትር መሾምይቻላል ግን በቀጥታ መሻር የማይሆን ነው። አከራካሪ ነውና!እንደ አታ አሳሞዋ እምነት ድሮውንም ዐቢይ ድርሻ ያበረከተው።

«ኢጋድ» ነበረናአሁንም ሁለቱን መሪዎች በመሽመገል ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸም ይችላል። እዚህ ላይ አሸባብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንግደ በፓርላማ አባላት ወይም በሚንስትሮች ም/ቤት አባላት ላይ ተጽእኖ አድርጎ ይሆን? ወይስ የሽግግሩ መንግሥት ድክመት ነው?

«ማናቸውም፤ ከአሸባብ ጋር በቀጥታ ግንኙነት አላቸው ብሎ ማመላከት ከባድ ነው። አጠቃላዩ የሽግግር ኺደት ይህን አይፈቅድምና! እንደሚሰማኝ፣ ይህ አለመጣጣምም ሆነ ክፍፍል ፣ ከአሸባብ ጋር ግንኙነት የለውም ፤ ዋናው መንስዔ የመንግሥት ደካማነት ነው።»

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic