ሶማልያና አሸባብ የዉስጥ ሽኩቻ | አፍሪቃ | DW | 29.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ሶማልያና አሸባብ የዉስጥ ሽኩቻ

የሶማልያ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ የመረጃ ኃላፊ እንደሆኑ የተነገረላቸዉ ግለሰብ ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ በሶማልያ ለሚገኝ የአፍሪቃ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይልና ለሶማልያ መንግሥት ጦር እጃቸዉን ከሰጡ በኋላ ግለሰቡ ከዓመት በፊት ቡድኑን ጥለዉ መዉጣታቸዉን አሸባብ ዛሬ አስታወቀ።

ዛካሪያ ኢስማይል ሄርሴ እጃቸዉን የሰጡት ባለፈዉ መስከረም በዩናይትድ ስቴትስ ሰዉ አልባ አውሮፕላን « ድሮን» ጥቃት ከተገደሉት የአሸባብ የቀድሞ መሪ አህመድ ጎዳኔ ታማኞች ጋር በመቃረናቸዉ ሳይሆን እንዳልቀረ ነዉ የተገለፀዉ። ከ2 ዓመት በፊት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ዛካሪያ ኢስማይልን ለያዘ ወይም ለጠቆመ 3 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቶ እንደነበር ይታወቃል። እንደ አሶስየትድ ፕሬስ ዘገባ በሶማልያ የሚንቀሳቀሰዉ አሸባሪ ቡድን አሸባብ፤ መዲና ሞቃዲሾ ውስጥ የነበረውን ይዞታ ከማጣቱም ባሻገር የሶማሊያ እና የኬንያ ስጋት በመሆን ተወስኗል። እጃቸዉን ለመንግሥት የሰጡት የአሸባብ የመረጃ ኃላፊ ዛካርያ ኢስማኢል ሄርሴ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ ተዘግቦአል። የአሸባብ ከፍተኛ የመረጃ ጉዳይ ተጠሪ እጅ መስጠት የቡድኑን መዳከምና መከፋፈል ጠቋሚ ይሆን? የፀጥታ ጥናት ተቋም በእንግሊዘኛ ምህፃሩ ISS የሰላምና የደሕንነት ጥበቃ ሪፖርት ኃላፊ ዶክተር ሰለሞን በየነ ደርሶ አነጋግረን ነበር። የአሸባብ ከፍተኛ የመረጃ ጉዳይ ተጠሪ እጅ መስጠት የቡድኑን መዳከምና መከፋፈል ጠቋሚ ይሆን? የፀጥታ ጥናት ተቋም በእንግሊዘኛ ምህፃሩ ISS የሰላምና የደሕንነት ጥበቃ ሪፖርት ኃላፊ ዶክተር ሰለሞን በየነ ደርሶ አነጋግረን ነበር።


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic