ስፖርት | ስፖርት | DW | 10.02.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ስፖርት

ባሳለፍነዉ ሳምንት በተካሄዱ የእግር ኳስ ዉድድሮች የአፍሪቃ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ይጠቀሳል።

በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት 24 የቅድመ ማጣሪያ ግጥሚያዎች ተካሂደዋል። በዚህም ደደቢት የዛንዚባር አቻዉን አሸንፎ ለመልስ ግጥሚያ ቀጠሮ ይዟል። ለአፍሪቃ ኮን ፌዴሬሽን የማጣሪያ ጨዋታ የቀረበዉ የመከላከያ ቡድን ግን በኬንያዉ ሌፐርድ ተሸንፏል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፤ የጀርመኑ ቡድንደስ ሊጋ እና የስፔኑ ላሊጋም ያልተጠበቁ ዉጤቶች የተመዘገቡበት ነበር።

ዓርብ ዕለት የተከፈተዉ ሩሲያ የምታስተናግደዉ የሶቺዉ የክረምት ስፖርት ቅዳሜ ዕለት በአሜሪካን የወርቅ ሜዳልያ አንድ ብሎ እስካሁን አንዳንዶች በርከት ያለ ሜዳሊያ ሲሰበስቡ ሌሎች እየተመለከቱ ነዉ። ኖርዌይ በሁለት የወርቅ በአንድ የብርና በአራት የነሃስ እየመራች ነዉ።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic