ስፖርት መጋቢት 4፤ 2009 ዓ.ም | ስፖርት | DW | 13.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

ስፖርት መጋቢት 4፤ 2009 ዓ.ም

በዛሬው ስፖርት አትሌቲክስ ፣ የአፍሪቃ እግርኳስ ሻምፕዮና ፣ የአውሮፓ ሻምፕዮን ሊግ ፣የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ የሜዳ ቴኒስ እና የብስኪሌት ውድድሮች ውጤቶች ተካተዋል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:55

ስፖርት 130317

 

ለ አትሊት ሞ ፋራህ የተሰጠውን እና  ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሳውን በፈሳሽ መልክ የሚወሰድ የአበረታች ውህድ መረጃ ምናልባት በአግባቡ አልተመዘገበም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል

ውህዱ የተሰጠው በ ወቅቱ የ ሞ ፋራህ አስልጣኝ በነበረው አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ትእዛዝ በ ብሪታንያ አትሊቲክስ የህክምና ቡድን  ነው ምንም አንኳን የብሪታንያ አትሊቲክስ ፊዲሪሽን  ለ አሚሪካው የፅረ አበረታች ንጥረነገር ኤጀንሲ የጠየቀውን መረጃ ሁሉ አሳልፎ የሰጠ ቢሆንም ሞ ፋራህ ከ2014የሎንዶን ማራቶን ውድድር በፊት ስለወሰደው ውህድ  ቁልፍ የህክምና መረጃ ሳይ መዘገብ እንደቀረ ማረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል ።ለአፍሪካ ሻምፒዮንስ ምድብ ለማለፍ ትላንት 10 ጨዋታዎች በተላያዩ የ አፍሪካ ከተሞች ተካሂደዋል ከነዚህ ውድድሮች መካከል አንዱ  ቅዱስ ጊዮርጊስ  የመጀመሪያ ጨዋታውን በኮንጎ ከ ክሊይፕርድ ጋር ኣድርጎ 1 ለ 0 አሸንፏል። ጎልዋ በ28 ደቂቃ በአዳነ ግርማ የተገኘች ስትሆን ጨዋታው ሊጠናቀቅ 10 ደቂቃ ሲቀረው አዳነ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል ::ውጤቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚዳው የሚያደርግው ቀጣይ ጨዋታ የተሻለ እድል እንዲኖረው ያደርገዋል

 ማላዊ ከ 2019 የ አፍሪካ ዋንጫ ከ 2018 ቻን ውድድር ራሱዋን ማግላልዋን አስታወቀች።

የማላዊ እግርኩዋስ ማህብር ውሳኔውን  ያስታወቀው የማላዊ መንግስት የውጭ አስልጣኝ አንደማይቀጥር በማስታወቁ ነው ።የእግርኳስ ማህበሩ  አስልጣኝ ለመቅጠር ከመንግስት ጋር 50

50ደመወዝ ክፍያ ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ከወራት ምክክር በሁዋላ መንግስት የስፖርት ሚንስትሩ ያቀረበው ሀሳብ ውድቅ በማድረጉ ነው፣የማላዊ እግርኩዋስ ፊዲሪሽን ራሱን ከመጭው ውድድር ያገለለው።

ሚዳው አስቸጋሪ በነበረው ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋርቶ መውጣቱ ሀሙስ  በሚዳው ኦልትራ ፎርድ  የሚያደርገውን ጨዋታ ተስፋ የተሞላበት አድርጎታል ዛሪ በስታንፍርድ ብሪጅ ላኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍፃሚ የቀድሞቡ ቡድናቸውን ቸልሲን የሚገጥሙት ጆሲ ሞሪኛ ሀሙስ በኤሮፓ ሊግ ከ ሮስቶቭ ጋር የመልሱን ጨዋታ ያደርጋሉ ።

የአለም ቁጥር አንድ የሜዳቴንስ ተጫዋች አንዲ መሪ በአስገራሚ ሁኔታ በህንድ ኦፕን የሜዳቴንስ ውድድር  ሁለተኛ ዙር ከውድድር ውጭ ሆኗል የ26 አመቱ ካናድዊ  ቮስክ ፖስፒስል  6ለ4 7ለ6 በሆነ ውጤት አሽንፎታል።

በሲቶች ተመሳሳይ ውድድር የብሪታንያ ቁጥር አንድ ጆዋና ኮንታ በካሮላይን ጋርሲያ 6ለ3 3ለ6 6ለ7 በሶስተኛው ዙር ተሸንፋ ከውድድሩ ውጭ ሆናለች  የህንድ ኦፕን የሜዳ ቴኒስ  ውድድር እስከ እሁድ ይቀጥላላል ።

210 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው  የአለም የጎዳና ላይ የብስክሌት ውድድር በጣልያን ትላንት ተካሂዷል ። ስሎቫኪያዊው የብስክሌት ተወዳዳሪ ፒተር ሳጋን አሽንፏል ፈረንሳዊው ቲቡት ፒኖት ሁለተኛ  ስሎቬያኑ ፕሪሞዝ ሶስትኛ ግራንት ቶማስ ከ ታላቅዋ ብሪታንያ አራተኛ ሆንዋል ።በፓሪስ  ኒስ በተካሂደ ሌላ የብስክሌት ውድድር ሰርጊዮ ሀኖ አሸንፎዋል።

ሀና ደምሴ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic