ስፖርት፤ መስከረም 2፤2009 ዓ,ም | ስፖርት | DW | 12.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

ስፖርት፤ መስከረም 2፤2009 ዓ,ም

በርዮ ፓራ ኦሎምፒክስ ኢትዮጵያ የመጀመርያዉን ሜዳልያ እሁድ እለት አግኝታለች። በማንችስትር ደርቢ ጆዜ ሞርኒዮ በዘንድሮዉ የእንጊሊዝ ፕሬሜር ሊግ ላይ ቀዳሚዉ ሽንፈታቸዉን ሲያስተናግዱ ባርሴሎናም በኑካንፕ ያልተጠበቀ ሽንፈት ደርሶበታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:29

ስፖርት፤ መስከረም 2 2009 ዓ,ም


የጀርመኑ ባየርሙኒክ ዘንድሮ ጅማሬዉ አምሮለታል። ክሪስትያኖ ሮናልዶም ከጉዳት አገግሞ ለቡድኑ ግብ ማደኑን ጀምሮአል። ለመጀመርያ ጊዜ ለሚካሄደዉ ለምሥራቅና መካከለኛዉ አፍሪቃ የሴቶች እግር ኳስ ቻንፔዮና ላይ ሉሲዎች ተካፋይ ይሆናሉ የሚሉትና ሌሎች ስፖርታዊ ርዕሶች በዕለቱ መሰናዶ የምንዳስሰዉ ይሆናል። ባለ,ዉ ረቡዕ በድምቀት በተከፈተዉና 16 ሃገራት ተካፋይ በሆኑበት በሪዮ ፓራ ኦሎምፒክስ ኢትዮጵያ የመጀመርያዉን የብር ሜዳልያ ባሳለፍነዉ እሁድ አግኝታለች። እሁድ ምሽት በተካሄደዉ የ 1500 ሜትር የሩጫ ዉድድር አትሌት ታምሩ ደምሴ በሁለተኝነት በማጠናቀቅ የብር ሜዳልያን አግኝቶአል። አልጀርያዊዉ ኑካ አብዱለቲቭ የዉድድሩ አሸናፊ በመሆን የወርቅ ሜዳልያን እኩ አስገብቶአል።

ሃይማኖት ጥሩነህ


አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic