ስፔንን ቀዉስ ዉስጥ የጣለዉ የመገንጠል ጥያቄ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 30.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ስፔንን ቀዉስ ዉስጥ የጣለዉ የመገንጠል ጥያቄ

ከ3 ሳምንት በፊት በስፔን ማዕከላዊ መንግስት እና በራስ ገዟ የካታላን አስተዳደር የተፈጠረዉ ዉዝግብ እና ሕገ መንግሥታዊ ቀዉስ በዚህ ሳምንት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ልክ የዛሬ ወር የግዛቲቱ መንግሥት ያካሄደዉንና አብዛኛዉ ሕዝብም ነፃነት መረጠ የተባለበትን ሕዝበ ዉሳኔ ማዕከላዊዉ መንግሥት ሕገ ወጥ ነዉ በማለት ያገደዉ መሆኑ የሚታወስ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:46 ደቂቃ

የመገንጠል አቀንቃኞችን የሚቃወሙ አደባባይ ወጥተዋል

የግዛቲቱ ፓርላማ ግን ባለፈዉ ዓርብ የምርጫዉን ዉጤት መሠረት አድርጎ የግዛቲቱን ነፃነት አዉጇል። የስፔን መንግሥትም የግዛቲቱን ባለስልጣኖች በመሻር በዛሬዉ ዕለት ክስ እንደሚመሠርትባቸዉ አስታዉቋል። የመገንጠል አቀንቃኝ የሆኑት የካታላን ባለስልጣናት ግን ለማድሪድ ትዕዛዝ ሆነ ማሳሰቢያ ቁብ የሰጡ አይመስሉም። ገበያዉ ንጉሤ ከብራስልስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic