ስጋት የተደቀነበት የሰሜንና የደቡብ ሱዳን የሰላም ውል | ኢትዮጵያ | DW | 22.08.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ስጋት የተደቀነበት የሰሜንና የደቡብ ሱዳን የሰላም ውል

የሞተው ሰው ቁጥር ሁለት ሚልዮን ደርሶዋል፤ የተፈናቀሉት ደግሞ አራት ሚልዮን። ከአንድ ሚልዮን ተኩል የሚበልጡ ስደተኞች በውጭ ሀገሮች ይኖራሉ። የደቡብ ሱዳን ደቡባዊ ከፊል የሀያ ሁለት ዓመቱ የርስበርስ ጦርነት እጅግ ተጎድቶዋል።

default

በዋው ከተማ የተሰማራው የተመደ ሰላም አስከባሪ ጓድ


ይኸው ጦርነት ከአምስት ዓመት በፊት እአአ በ 2005 ዓም በሱዳን መንግስትና በደቡብ ሱዳን ህዝብ ነጻ አውጪ ጦር መካከል በናይቫሻ ኬንያ በደረሱት የሰላም ስምምነት ሊያበቃ መቻሉ ይታወሳል። በሰላሙ ስምምነት እንደሰፈረው፡ የደቡብ ሱዳን ህዝብ ውሉ ከተፈረመ ከስድስት ዓመታት በኋላ እአአ በ 2011 ዓም በሬፈረንደም ከሱዳን ጋር በመቆየቱ ወይም ነጻ መንግስት በመመስረቱ ጥያቄ መካከል መወሰን ይጠበቅበታል። ይሁንና፡፡ይኸው የህዝበ ውሳኔ ዕለት እየተቃረበ በመጣ ቁጥር፡ ባካባቢው አዲስ ጦርነት እንዳይነሳ የሚታየው የህዝቡ ስጋት ከፍ እያለ ሄዶዋል።

ዳንየል ፔልስ/አርየም ተክሌ

MM

Audios and videos on the topic