ስጋት ባጠላባት ኢትዮጵያ የምሁራን ሚና | ኢትዮጵያ | DW | 07.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ስጋት ባጠላባት ኢትዮጵያ የምሁራን ሚና

ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት ለአንዳንዶቹ ተስፋ ለአንዳንዶቹ ስጋት ለቀሪዎቹ ዕድል ከፊቷ ያለ አይነት ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ይታይ ከነበረው ሕዝባዊ አመፅ እና የመንግሥት የኃይል ርምጃ በመነሳት ሀገሪቱ ወደከፋ አቅጣጫ ልትሄድ ነው የሚሉ ትንተናዎች እና ፖለቲካዊ ትንበያዎች ከሽፈው ያልተጠበ ለውጥ ከታየባት አንድ ዓመት ሆነ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:24

«የለውጡ ሂደት በግጭቶች እና መፈናቀሎች ታጅቧል»

ለውጡ ብዙዎች ያልጠበቁት መሆኑ ብቻ ሳይሆን በተከታታይ አዎንታዊ ርምጃዎች በመታጀቡ የዓለም መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቦ ሰንብቷል። ተስፋና እፎይታው እንዳለ ሆኖ ለዓመታት ተዳፍኖ የቆየው የማንነት እና የወሰን ጥያቄ በዜጎች መካከል መገፋፋት እና መጋጨትን አስከትሎ በአራቱም አቅጣጫ ሞት እና መፈናቀል ማስከተሉ ስጋትን ማምጣቱ ይታያል። በዚህ መሃል በተለያዩ መድረኮችም ሆነ በማኅበራዊ መገናኛው የተማሩ የሚባሉ ወገኖች የሚሰነዝሯቸው ሃሳብ አስተያየቶች ውጥረቱን እያባባሰ ሀገር እንደሀገር የመቀጠሏን አሳሳቢ እያደረገው መምጣቱን ብዙዎች ይስማማሉ። DW ዶይቼ ቬለ እንዲህ ባለ ወቅት የምሁራን ሚና ምን መሆን አለበት ሲል እንግዶች ጋብዞ አወያይቷል። ሙሉ ውይይቱን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ 

 

 

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች