ስደትና የጀርመን ሥራ ገበያ | ባህል | DW | 23.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ስደትና የጀርመን ሥራ ገበያ

በጦርነትም ሆነ በሌሎች የተለያዩ የፖለቲካ ቀዉሶች ተሰዶ ወደ ጀርመን አገር የሚፈልሱት ስደተኞች ቁጥር 1,5 ሚልዮን ሊደርስ እንደሚችል ተገምቶአል። ተገን ጠያቂዎች ወደ ጀርመን መምጣታቸዉንና የጀርመንን ኑሮ እንዴት ይገልፁታል። ወጣት የጀርመናዉያንስ ይህን ጉዳይ እንዴት ያዩታል?

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:12

ስደትና የጀርመን ሥራ ገበያ

ስሙ «ባሃ ትፔት» ይባላል፣ የ21 ዓመት ወጣት ነዉ። ባለፈዉ ዓመት በያዝነዉ ወር ከጋና ተሰዶ ወደ ጀርመን አገር መምጣቱን ይናገራል። ከጋና ብቻ ሳይሆን በመቶና በሽ የምቆጠሩ ስደተኞች ከናይጄርያ፣ ከኤርትሪያ፣ ከኢትዮጵያ ፣ከሶርያ፣ ከአፍጋንስታን፣ ከኢራቅ፣ ከፓኪስታን፣ አልፎም ከባልካን አገሮች ወደ ጀርመን አገር ይሰደዳሉ። እየተገባደደ ባለዉ በጎርጎርዮሳዊዉ አቆጣጠር በ2015 ዓ,ም ወደ ጀርመን አገር የሚፈልሰዉ የስድተኛ ቁጥር እስከ 800,000 እንደሚደርስ የጀርመን የአገር አስተዳደር ሚኒስትር ቶማስ ድ ማዚሬ፣ መናገራቸዉ ይታወቃል። ሽፕጌል የተሰኘዉ የጀርመን መጽሔት ጥቅምት ዉስጥ ባስነበበዉ ዘገባ ጀርመን ይደርሳሉ ከተባለዉ ስደተኛ መካከል እስካለፈዉ መስከረም ወር ድረስ ብቻ 577,307 ስደተኞች መመዝገባቸዉን ይፋ አግርጓል። ከነዚህ ስደተኞች መካከል ደግሞ እስከሁን 303, 443 ጥገኝነት ጠይቀዉ 174, 545 ቱ የጥገኝነት ጥያቄያቸዉ ተቀባይነት ማግኘቱን አሳይቶአል። ወደ ጀርመን ይደርሳሉ ተብሎ ከተገመተዉ ስድተኞች መካከል ከግማሽ በላይ እድሜያቸዉ ከ16-35 መሆኑንም የጀርመን የፍልሰትና የስድተኞች ጉዳይ መሥርያ ቤት አስታዉቋል።

ከጦርነትና ከሌሎች የተለያዩ ቀዉሶች ተሰደዉ የሚመጡት ወደ 100,000 ከሚሆኑት ፍልሰተኞች መካከል 13 በመቶዉ የሚሆኑት ኮለጅ ያጠናቀቁ መሆናቸዉን ፍራንክፉርት አልጌማይን ጋዜጣ መዘገቡ ይታወቃል። ቁጥር ከቃል በላይ ይናገራል እንደታባለዉ ይህ የስደተኞች ፍልሰት የጀርመን ወጣቶች እንዴት ነዉ የምያዩት? እሄን አስመልክቶ በቦን ዩንቨርስቲ ት የመጀመርያ ዓመት የሕግ ሞያ ተማሪ የሆነዉ የ18 ዓመቱ ወጣት ያን ስናጋር፣«አብዛኞቹ ምዲያዎች ስለ ስደተኞች ብዙ ዘግቦዋል። እንደ አድማጭ ወይም እንደ ተመልካች እየሆነ ያለዉ ነገር ያሳዝናል። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ወደ ጀርመን አገር ለመምጣት ብዙ ችግሮችን አይተዉ ነዉ። በእርግጥ ትልቅ ችግር ነዉ ባልልም ግን ፈተና ሊሆን የሚችለዉ ስደቶኞቹን ወደ ማኅበረሰቡ ማዋሃድ መሞከር ላይ ነዉ ብዬ አስባለሁ፣ ምክንያቱም ኣብዛኛዎቹ እነዚህ ስደተኞች የተማሩ ሲለሆኑና በእርግጥም ወደ የመጡበት አገር መመለስ የማይታሰብ በመሆኑ ወደ ማህበረሰቡ ማዋድ ግዴታ ነዉ።»

ይህ ወደ ጀርመን የገባዉ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ስደተኛ የአገሪቱን የስራ ገበያና አልፎም የአገሪቱ ባህል ላይ ጉዳት ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ስጋት ቢያሳድርም፣ በተቃራኒ ጥቅም አለዉ የሚሉም አልጠፉም። እንደ ሽፕጌል ዘገባ ከሆነ በአገሪቱ 2,8 ሚሊዮን ነዋሪ ሥራ አጥ ቢሆንም፣ ስደተኞች ሥራ ማገኘታችዉ መንግስት ለነሱ የምሰጠዉን ገንዘብ በጀት በመቀነስ ረገድ አስተዋጾ እንዳለዉ ያብራራል። እንደዛም ሆኖ ግን አንድ ቀኝ-ዘመም ፓርቲዎች ለምሳሌ የጀርመን ብሔራዊ ድሞክራቲክ ፓርቲ (NPDን) ጨምሮ ፀረ-እስልምና አቋም ያለው በምህፃሩ ፔጊዳ የተባለው ንቅናቄ ስደተኞች ወደ አገራቸዉ ወደ ጀርመን መፍለስ የሥራ ገበያዉን እንደተቀራመትዋቸዉ ያህል ነዉ መፈክራቸዉን የምያሰሙት። ይህን ሃሳብ ግን ቤን የተባለዉ የ18 ዓመት ወጣት እንደማይጋራ ነዉ የሚናገረዉ፣«ሃሳቡን አልጋራም። በአጠቃላይ በዓለም ላይ የሚገኘዉ የተትረፍረፈ ሃብት ያለአግባብ ተከፋፍሎአል ብዬ ነዉ እኔ የምስበዉ ፣ ለዚህም በእርገጠኝነት እነዝህ ስደተኞች እዚህ መምጣጣቸዉን ና ሥራ መፈለጋቸዉ ጥሩ ሆኖ ኣግኝቸዋለዉ። ያ ችግር ነዉ ብዬ አለስብም። መጀመርያ ላይ ለአጭር ጊዜ ስደተኞቹ ሊቸገሩና ልጨናነቁ ይችላሉ። ሆኖም ግን በረጅም ግዜ ዉስጥ መፍቴ ልያገኝ ና ሁለቱም ወገኖች ሊጠቀሙ ይችላሉ ብዬ ኣስባላዉ።»

አንድአንድ የስራ ሰጭ ግለሰቦች ለደርሽፒግል ጋዝጣ ሲናገሩ፣ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ብቃት ያላቸዉን ሰራተኛ ማግኘት እንደከበዳቸዉ ከጠቀሱ በዋላ ኣሁን ከባልካን እና ከለሎች ቦታዎች ተሰዶ የምመጡትን እየቀጠሩ መሆናቸዉንም ያብራራሉ። ለስራ ማንኛዉም የሰዉ ቆዳ ቃለምን ሳንለይ እንኳን ደህና መጡ ነዉ የምንላቸዉ፣ የተቀረዉ ሌላዉ ነገር ግን ኣላስፈላጊ ነዉ። የሕግ ተማሪዉ ያን ስደተኞች ስራ እየወሰዱብን ነዉ የምለዉን አሳብ ዉድቅ ካደረገ በኋላ፣ ሥራ ቀጣሪዎች በሥራ ቦታ ላይ ስደተኞቹን በእኩል ዓይን ማስታናገድ እንዳለባቸዉ ይናገራል፤«ስደተኞች ሥራ እየወሰዱብን ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ከሁኑ መተምበይ በጣም ከባድ ነዉ። ምክንያቱም፣ በእርግጥ የኤኮኖሚዉን ጉዳይ ከግምት ዉስጥ ማስገባት ቀዳሚ ቢሆንም የተሻለ የሰዉ ሃይልን ለሚገባዉ ሥራ ቦታ ላይ ለማስቀመጥ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጅ፣ ስደተኞችን በተመለከተ፣ ለነሱ የምገባዉን የሥራ ገበያ በኤኮኖሚዉ ዉስጥ ተፈልጎ ያለ ምንም አድሎ ሊሰጣቸዉ ይገባል። ለስደተኞች ተገቢዉን እድል መስጠት በጣም አስፈላጊ ነዉ። ግን ከወዲሁ ቀደም ብሎ ወደ ጀርመን የምመጡ ስደተኞች ሥራ ሊነጥቁን ነዉ ብሎ ከመፍራት በፊት ሥራ አጦች ሥራ በራሳቸዉ ኃይል ፈልገዉ ለማግኘት መጣር ያስፈልጋል።»

ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያላዉ ስደተኛ ከጦርነት፣ ከፖለቲካ ጫናዎች ኢንድሁም የኤኮኖሚና የማኅበራዊ ችግሮች ተዳርጎ አገሩን ጥሎ የሚሰደድ ነዉ። ይሁን እንጅ ጀርመን አገር ምድረ-ገነት ሆናቸዋለች። ለዛም ነዉ፣ ጋናዊዉ ባሃ ትፔት ጀርመን የመቆየት ፍላጎቱን በዳስታ የሚገልፀዉ፣ ሆኖም ግን አሁንም ችግሮች ኢንደምያጋጥሙት ለዶቼ ቬሌ ሳይጠቅስ አለፈም፣ «አዎን፣ በጀርመን አገር መኖር ይፈልጋለሁ። ግን ችግሩ፣ እዚህ አገር ከመጣሁ በኋላ የመኖርያ ፍቃድ ልሰጠኝ ይገባ ነበር። አሁን ትምህርት ቤት እየሄድኩ ነዉ። ግን ምንም ጥቅማ ጥቅምን እያገኘሁ አይደለዉም። ጥቅም ማግኘት ይኖርብኛል፣ ያኔ ግን ምን እየሰራዉ መሆኔን አዉቃለዉ። ከጣሊያን ወደ ጀርመን ስመጣ፣ እዛ ኑሮ ከባድ ብሆንም፣ መጀመርያ ወደ ትምህርት ቤት ትላካለህ፣ ከዛም በኋላ የአጭር ግዜ ሥራ ይሰጠን ነበር።»

የጀርመን የአገር አስተዳደር ሚኒስትር ቶማስ ዴ ሚዝየር ወደ ጀርመን ይገባሉ ብለዉ የገመትዋቸዉ ወደ 800,000 የሚሆኑ ስደተኞች ቢሆኑም፣ በቦን ከተማ ጀርመን በሚገኘዉ የስዉ ኃይል ጥናት ተቋም ዳይሬክተር አሌክሳንዴር ሽፔርማን እንደሚሉት ይህ ቁጥር በዓመቱ መጨረሻ ወደ 1.5 ሚልዮን ልጠጋ እንደምችል ተናግረዋል። ይሁን እንጅ የስዉ ሃይል ጥናት ተቋም ዳይሬክተሩ አሌክሳንዴር ሽፔርማን ወደ ጀርመን የሚመጡት ስደተኞች ሥራ ይቀሙናል የሚል ስጋት ቢኖርም፤ ስደተኞቹን በሥራ ገበያ ከማቀላቀል በፊት መጀመርያ መወሰድ ያለበት እርምጃ ስደተኞቹን ከማኅበረሰቡ ጋር ማዋድ ነዉ ብለዋል። ስደተኛዉም ሆነ ጀርመናዉያኑ አገሪቱ እንድታሟላላቸዉ የሚመኙትና የሚፈልጉት ነገር አለ። ይሁን እንጅ ይህ ምኞትና ፍላጎት መስተካከል እለበት ይላሉ አሌክሳንደር።«በሁለቱም በኩል ይሆናል ብለዉ የሚጠብቁትን ማስተካከል በጣም አስፈላጊ ነዉ። መጀመርያ ስደተኞቹ ይሆናል ብለዉ የሚጠብቁት አነሰም በዛ፤ በአገሪቱ ብዙ መብት ብዙ ደንነትና ብዙ ክፍት የስራ ቦታ በጀርመን እንዳለ አድርገዉ ነዉ የሚወስዱት። ይህ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ እዉነትም ነዉ፣ ግን ያን ለማገኛት ትግስት ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም መጀመርያ የጀርመንኛ ቋንቋ መማር አለባቸዉ። እሱንም መማር ቀላል አይደለም። ከዛ በኋላ ለሥራ ገበያዉ የምያስፈልገዉን ብቃት መያዝ አለባቸዉ። በሌላ በኩል፣ በአሁኑ ግዜ ጀርመኖች ከፍተኛ ቁጥር ያላዉ ስደተኛ ወደ አገራቸዉ መምጣቱን ሊፈሩ ይችላሉ፣ ይሁን እንጅ በአሁኑ ግዜ ሥራችንን በትክክል ለመስራት የምያስችለን ብዙ የግልና የመንግሥት መዋለ ንዋይ አፍሳሾች እንደምያስፈልገን ማወቅ ይኖርባቸዋል። ስደተኞቹን ለመቀበልና ወደ ጀርመን ኅበረተሰብ ለመቀላቀል አልፎም የስራ ገበያዉ ዉስጥ ለማስገባት የገንዘብ አቅምና የሰዉ ሀይል አለን።»

የጀርመን ፌዴራል መንግስት የቅጥር ምርምር ተቋም ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ይፋ ያደረገዉ ጥናት እንደምያሳየዉ፣ እድሜያቸዉ ከ15 እስከ 64 የምሆኑ ስደተኞች 8 በመቶ በመጡበት ዓመት ስራ ያገኙ ስሆን፣ 50 በመቶ ደግሞ በሚቀጥሉት አምስት ዓመት ዉስጥ ሥራ የማግኘት እድል እንዳላቸዉ ይጠቅሳል። ይህ ቁጥር በሚቀጥሉት 15 ዓመታት ዉስጥ 70 በመቶ ሊደርስ እንደምችል ነዉ የተጠቀሰዉ። ጥናቱ ባለፈዉ ሐምሌ ወር ወደ 589,000 ክፍት የሥራ ቦታ መኖሩ አሳይቶ በሚቀጥሉት 15 ዓመታት ዉስጥ 36 ሚሊዮን ገደማ በሥራ ገበያዉ የሥራ ማግኘት እድል ሊፈጥር እንደሚችል ጥናቱ ያይዞ ይጠቁማl ያሳያል።

መጀመርያ እነዚህ ስደተኞች ጀርመንን መምረጣቸዉ የሚገርም ነዉ ይላሉ የስዉ ሃይል ጥናት ተቋም ዳይሬክተሩ ኣሌክሳንዴር ሽፔርማን ለዶቼ ቬሌ እንደተናገሩት፣። ይሁን እንጅ በሥራ ገበያዉ ስደተኞቹ ምን ያህል ድርሻ እንዳላቸዉ አስመልክቶ ሲናገሩ«በአሁኑ ግዜ የጀርመን ሥራ ገበያ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነዉ ያለዉ፣ ያ ማለት የሥራ አጥነት ቁጥር በጣም የቀነሰ ሲሆን የሥራ እድል በጣም ከፍተኛ ሆንዋል። በአሁኑ ሰዓት ወደ 500,000 ክፍት የሥራ ቦታዎች አሉ። ይህ ሲታይ ብዙ የሥራ እድል ወደ ጀርመን ለተሰደዱት ስደተኞቹ ያለ መስሎ ሊታይ ይችላል። ግን እዉነቱን ለመናገር ይህ ትክክል አይደለም፣ ይህ ክፍት የሥራ ቦታን ማሙዋላት ከባድ ነዉ፣ ምክንያቱም ጀርመን የራሱዋ ሥራ አጦች ስላሉዋትና ሥራም ኖሮዋቸዉ የተሻለ ሥራ ፈላጊዎች በመኖራቸዉ ነዉ።»

በእርግጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ስደተኞች መምጣጣቸዉ ለጀርመን ህዝብ ፈተና ሊሆን ይችላል። በየአከባቢዉ ያሉት ባለስልጣናቶች ስደተኞችን ለመቀበልና መጠለያ ቦታዎችን ለማዘጋጀት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። ለዚህም ምክንያት በአገሪቱ በጀት ላይ በቢሊዮኖች የምቆጠር ገንዘብ እንደሚጨመረም የሚዲያ ዘገባዎች ያሳያሉ። በከፍተና ከፍተኛ ቁጥር ይህን ያህል ስደተኛ ተያይዞ መምጣቱ ለጀርመን አዲስ አይደለም ሲል ዴር ሽፕጌል የተሰኘዉ መፅሔት በዘገባዉ አትቶአል። ከጎርጎርሮሶያን አቆጣጠር 1960 ዓ,ም አጋማሽ ጀምሮ ጀርመን የስደተኞች መጠለያ ብትሆንም ፤ እስካሁን ዘመናዊ የስደት ሕግ እንደሌላት ነዉ የተጠቀሰዉ።። ይሁን እንጂ፣ ከቅርብ ወራት ወዲህ የጀርመን የሕግ አርቃቅዎች ጥገኝነትን ለሚጠይቁ ስደተኞች ወደ ሥራ ገበያ ለማዋሃድ፣ ሕጉ የያዘዉን አንደ አንደ የስደት አንቀፆች እያሻሻሉ መሆኑንም ኣብራርተዋል። ስደተኞችን ወደ ሥራ ገበያዉ ለመቀላቀል መንገዱ ቀላል ባይሆንም፣ የሕግ አርቃቂዎቹ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ ለጋናዉ ባሃ ቲፔትም ሆነ እንደሱ የተሻለ ኑሮ በጀረመን አገር ለሚሹት ሁሉ ይህ የምስራች ዜና ነዉ የሚሆነዉ ።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic