ስደተኞች ከሊባኖስ ወደ ጣልያን ተጓጓዙ | ዓለም | DW | 05.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ስደተኞች ከሊባኖስ ወደ ጣልያን ተጓጓዙ

የጣልያን መንግሥትና የኃይማኖት ተቋሞች በመተባበር በሊባኖስ ከሚገኘዉ የስደተኞች ጣብያ 101 ስደተኞችን ወደ ጣልያን ማምጣታቸዉ ተመለከተ።

የአንጌሊካዉያን አብያተ ክርስትያናት ፊደሪሽንና የቅዱስ ኢጂዲዮ ማኅበረሰብ በመተባበር አራት ኢራቃዉያንን ጨምሮ እና 97 101 የሶርያ ስደተኞችን ቤሩት ሊባኖስ ከሚገኝ የስደተኞች ጣብያ ወደ ጣልያን አስገቡ። የጣልያን መንግሥትና እንዚህ ተቋማት ባለፈዉ የካቲት ወር ላይ ዘጠና ስደተኞችን ከሊባኖስ ማስመጣታቸዉ ይታወቃል። የጣልያን መንግሥት ስደተኞቹ ወደ ጣልያን እንዲገቡ የቪዛ ፈቃድ ከመስጠት ዉጭ በፋይናንስ ረገድ ርዳታ እንደማይሰጥ ነዉ የተመለከተዉ። ጣልያን ሮም የሚገኘዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል።

ተክለዝጊ ገ/እየሱስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic