ስደተኞችን በመግደል የተጠረጠሩ መያዛቸዉ | አፍሪቃ | DW | 24.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ስደተኞችን በመግደል የተጠረጠሩ መያዛቸዉ

በደቡባዊ ጣሊያን በሲሲሊ ግዛት የካታኒያ ከተማ ፖሊስ ከሊቢያ ወደጣሊያን ያቀኑ የነበሩ ስደኞችን የጫነች ጀልባ ዉስጥ ስደተኞችን ገድለዉ ባህር ዉስጥ በመወርወር የተጠረጠሩ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታዉቋል።

በጩቤ ተወግተዉና ተደብድበዉ ወደባህር የተወረወሩት ቁጥር ወደስልድሳ እንደሚጠጋ ጀልባዉ ዉስጥ የነበሩ የዓይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ የገለፀዉ የካታኒያ ፖሊስ በደቡባዊ ላምፔዱዛ ከጀልባዉ ሞተር ከሚወጣዉ መርዛማ ጭስ የተነሳ መተንፈስ ሳይችሉ ቀርተዉ በመታፈን 29ሰዎችም መሞታቸዉንም አመልክቷል። ከስደተኞቹ የአንዱ ሕይወትም በካርቦን ሞኖክሳይድ ታፍኖ ወደሃኪም ቤት ሲወሰድ ማለፉም ተገልጿል።

ተኽለእዝጊ ገ/ኢየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic