ስደተኞችን ለማገድ፤የስጳኝ ልምድ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 22.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

  ስደተኞችን ለማገድ፤የስጳኝ ልምድ

እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2006 ከ30 ሺሕ በላይ ስደተኞች ከሴኔጋል ስጳኝ ገብተዉ ነበር።አብዛኞቹ የሴኔጋል ዜጎች ናቸዉ።ይሕ የሩቅ ትዉስታ ነዉ።ዛሬ ዝር የሚል የለም።በሴኔጋል የስጳኝ አምባሳደር አልቤርቶ ቪሬላ እንደሚሉት መንግሥታቸዉ ለዚሕ ዉጤት የበቃዉ ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በመስማማቱ ነዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:54

  ስደተኞችን ለማገድ፤የስጳኝ ልምድ

የአዉሮጳ ባለሥልጣናት የአፍሪቃ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ እንዳይገቡ ለመከላከል የሚደርጉት ጥረትና ዉይይት ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ለየስደተኞቹ የትዉልድ ሐገራት ድጋፍ ካልተደረገ የሰዎችን ፍልሰት መከላከል እንዳማይችል አዉሮጶች ይስማማሉ።በዚሕ ረገድ ስጳኝ የተሳካለት መስላለች።የዛሬ አስር ዓመት ግድም በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ የሴኔጋል ዜጎች በካነሪ ደሴት በኩል ወደ ስጳኝ ይገቡ ነበር።ዛሬ አድም ስደተኛ በካነሪ ደሴት በኩል ስጳኝ አይገባም።ስጳኝ ስደተኞቹን ማስቆም የቻለችዉ ከሴኔጋል ጋር ባደረገችዉ ሥምምነት ነዉ።ለተቀሩት የአዉሮጳ ሐገራት ጥሩ አብነት ይሆን? ይጠይቃል ማርክ ዱገ።ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።

ካፒቴን አንቶኒዮ ኩቬዶ ዳካር ወደብ ከቆመችዉ  የፖሊስ ጀልባ ላይ ሆነዉ ወደ ባሕሩ ይቃኛል።አንዲት መርከብ እየቀረበች መጣች።ሁለተኛዋ ተከተለች።ሁለቱም የስጳኝ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች  መርከቦች ናቸዉ።ሁለቱም የስጳኝና የሴኔጋል ፖሊሶችን አሳፍረዋል።ባሕሩን ይቃኛሉ።«በየቀኑ ከስምንት እስከ 10 የሚደርሱ መርከቦች እናያለን።አንድ ሁለቱ ያጠራጥራሉ። እንፈትሻለን።» ካፒቴን ኩቬዶ ናቸዉ-እንዲሕ ያሉት።«ብዙዎቹ አሳአጥማጆች ናቸዉ።ባሁኑ ጊዜ ስደተኛ አሳፍሮ የሚጓዝ ብዙም የለም።»አከሉ ካፒቴኑ።

                          

«ባሁኑ ጊዜ ባሕሩን ለማቋረጥ መሞከር ዋጋም የለም።የሚሞክሩትን እንይዛቸዋለን።አንዳዴ ከሩቅ የመጡ ሰዎችን እንይዛለን።ባለፉት ሁለት ዓመታት በጀልባ ወደዚሕ ወደ ሴኔጋል ወይም ወደ ሞሪታንያ ለመምጣት የሚሞክሩ አሉ።እነዚሕ ሰዎች ብዙ ገንዘብ ይከፍላሉ።መጨረሻቸዉ ግን እኛ እጅ ላይ መዉደቅ ነዉ።»

እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2006 ከ30 ሺሕ በላይ ስደተኞች ከሴኔጋል ስጳኝ ገብተዉ ነበር።አብዛኞቹ የሴኔጋል ዜጎች ናቸዉ።ይሕ የሩቅ ትዉስታ ነዉ።ዛሬ ዝር የሚል የለም።በሴኔጋል የስጳኝ አምባሳደር አልቤርቶ ቪሬላ እንደሚሉት መንግሥታቸዉ ለዚሕ ዉጤት የበቃዉ

ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በመስማማቱ ነዉ።«የስደተኞችን (ቁጥጥር) በተመለከተ የስጳኝ መርሕ ዉጤታማ የሆነዉ ከአካባቢዉ ሐገራት ጋር በተለያዩ መስኮች ተባብራ በመስራትዋ ነዉ።ይሕ ማለት፤ ድሕነትን በመዋጋት፤ ምጣኔ ሐብትን በማሳደግ፤ የንግድ እና የባሕል ልዉዉጥን በማጠናከር ረገድ መተባበር ማለት ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት ስደተኞችን መቆጣጠር ከፈለገ የስደተኞቹን ሐገራት ተጠቃሚ ማድረግ አለበት።»

 

ስምምነቱ  ለስጳኝ ጠቅሟል።ወይም የጠቀመ መስሏል።ለተቀሩት የአዉሮጳ ሐገራትም ጥሩ አስተምሕሮ ሊሆን ይችላል።ግን እንዴት?ሴኔጋላዊዉ የስደተኞች ጉዳይ አጥኚ አልይ ታንዲያን ከስምምነቱ ዋናዉን ያስረዳሉ።«ስደተኞቹን ለመግታት ስጳኝ ለሴኔጋል ባንዴ 20 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት ቃል ገባች።ሴኔጋል በዚያን ወቅት የምርጫ ዘመቻ ላይ ነበረች።ባንድ ጊዜ ብዙ ገንዘብ ተገኘ።ፕሬዝደንት ዋዴ በድጋሚ ተመረጡ።»ከገንዘቡ የተወሰነዉ ለምርጫ ዘመቻ ለመዋሉ አጥኚዉ እርግጠኛ ናቸዉ።ከተረፈዉ ገንዘብ ገሚሱ፤ የሴኔጋል ፖሊሶችን ለማሰልጠኚያ፤ ለአበል እና የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ለመግዢያ ዉሏል።

ታዲያ ማድሪድና ዳካር ድሕነትን ነዉ የተዋጉት ወይስ ድሐ ስደተኞችን?ይጠይቃሉ የመብት ተሟጋቾች።የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ባልደረባ ኤስቴባን ቤልትራን እንደሚሉት

ደግሞ የስጳኝ መርሕ ለስደተኞቹ መንገድ አረዘመባቸዉ እንጂ ስደትን አልቀነሰም።«ስጳኝ መግባት የሚፈልጉ ሰዎች አሁን በሞሮኮ ወይም በሊቢያ በኩል ይጓዛሉ።በፊት መተላለፊዋ ሴኔጋል ነበረች።አሁን ማሊ ሆናለች።»በርግጥ የሜድትራኒያን ባሕር አቋርጠዉ አዉሮጳ ከሚገቡት ስደተኞች ሴናጋላዉያን ከፍተኛዉን ቁጥር ይይዛሉ።የአስር ዓመቱ ቁጥጥርስ እስከ መቼ ይቀጥላል።ካፒቴን ኩቬዶ ፈገግ ይላሉ ጥያቄዉን ሲሰሙ።

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

 

 

 

Audios and videos on the topic