ስደተኞችና የባህር ጠረፏን ጥበቃ ያላረጋገጠችው ሊቢያ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 08.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ስደተኞችና የባህር ጠረፏን ጥበቃ ያላረጋገጠችው ሊቢያ

ባለፉት አራት ወራት ብቻ ከ1,600 የሚበልጡ ስደተኞች ሜድትሬንያን ባህርን አቋርጠው ወደ አውሮጳ ለመግባት ሲሞክሩ ህይወታቸው አልፋለች። በአደገኛው የባህር ጉዞ የሚሞቱት ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ ከመጣ ወዲህ፣ የአውሮጳ ሀገራት መሪዎች ለዚሁ አሳሳቢ ውዝግብ መፍትሔ ፍለጋ ባለፈው ሳምንት ጉባዔ አካሂደዋል።

18394915በዚሁ ጉባዔ ላይ ለስደተኞቹ መርጃ ተጨማሪ ገንዘብ ለመመደብ እና በሕገ ወጦቹ ሰው አሸጋጋሪዎች አንጻር ርምጃ ለመውሰድ መስማማታቸው ይታወሳል። ይሁንና፣ ስደተኞቹ በብዛት የሚነሱባት ሊቢያ የባህር ጠረፏን እንኳን በሚገባ የመጠበቅ አቅሙ ተጓድሏት ትገኛለች።

ሜሪሊን ዲውማ/ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

DW.COM

Audios and videos on the topic