ስደተኞችና አደገኛው የባሕር ላይ ጉዞ | አፍሪቃ | DW | 30.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ስደተኞችና አደገኛው የባሕር ላይ ጉዞ

ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት በምህፃሩ IOM ባወጣው ዘገባ ባሳለፍነው የጎርጎሪዮሳዊው 2013 ዓመት በርካታ የሶሪያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ ስደተኞች በአደገኛ የባሕር ላይ ጉዞ አውሮጳ መድረሳቸውን አትቷል።

ከስደተኞቹ አብዛኞቹ አውሮጳ የገቡት በኢጣሊያዎቹ የላምፔዱዛና የሲሲሊደሴቶች እንዲሁም በትንሿ አውሮጳዊት ሀገር ማልታ በኩል ነው። ስደተኞችን በተመለከተ አበሻ ኤጀንሲ የተሰኘው ስደተኞችን የሚረዳ ግብረ ሠናይ ድርጅት ኃላፊ አባ ሙሴ ዘርዓይ ለዶቸቬለ abeራሪያ ሰጥተዋል

ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት በእንግሊዘኛ ምኃፃሩ IOM በቅርቡ ይፋ ያደረገው ዘገባ 45 ሺህ ስደተኞች ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በሜዲትራኒያን ባሕር ወደ አውሮጳ መግባታቸውን ጠቅሷል። ከእነዚህ ስደተኞች መካከል 11,300 የሚሆኑት ጦርነት ካዳቀቃት ሶሪያ የፈለሱ ናቸው። 3,200 የሶማሊያ 9, 800 ደግሞ ከኤርትራ።

የጎርጎሪዮሳዊው ዓዲስ ዓመት ከገባ ወዲህ እንኳን በእዚህ አንድ ወር ውስጥ የባሕሩን ቅዝቃዜ ተቋቁመው የተወሰኑ ኤርትራውያን አውሮጳ መድረሳቸውን አባ ሙሴ ዘርዓይ ገልፀዋል። ሆኖም ስደተኞቹ አብዛኛውን ጊዜ መዳረሺያቸው በሆነችው ጣልያን የሚገጥማቸው አያያዝ ጥሩ ባለመሆኑም ወደ ሌላ የአውሮጳ ሃገራት ለዳግም ስደት እየተዳረጉ መሆናቸውን አባ ሙሴ አያይዘው ጠቅሰዋል።

በስደት አደገኛውን የባሕር ጉዞ ፈጽመው አውሮጳ ከገቡ ስደተኞች መካከል ከኤርትራውያኑ በተጨማሪ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ፣ እንዲሁም ሌሎች የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት ሰዎችም እንደሚገኙበት አባ ሳሙኤል ተናግረዋል።

ከጥቂት ወራት በፊት ላምፔዱዛ አቅራቢያ በእሳት ተያይዛ በነደደችው ጀልባ ላይ ተሳፍረው ከነበሩ ስደተኞች መካከል 360 በላይሰዎች ሲያልቁ አብዛኛዎቹ ኤርትራውያን መሆናቸው ይታወሳል።

ሙሉ ጥንቅሩን የድምፅ ማጫወቻውን በመጫን ያድምጡ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሂሩት መለሰ

ተዛማጅ ዘገባዎች