ስኮሊኦስስ እና ኪፎሲስ | ጤና እና አካባቢ | DW | 31.08.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

ስኮሊኦስስ እና ኪፎሲስ

የጀርባ አጥንት ወይም ህብለ ሰረሰር በተለያዩ ምክንያቶች የመጉበጥ እክል ሊገጥመው ይችላል። አንዳንዱ በዕድሜ ሂደት የህብለ ሰረሰር መጎዳት ምክንያት ይኽ ችግር ሲያጋጥመው በልጅነት ዕድሜ፤ አንዳንዴም እንዲህ ሆኖ የሚወለዱ ልጆች ሊኖሩ እንደሚችሉ የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:40

የጀርባ አጥንት ጉብጠት

በህክምናው ሳይንስ አጠራር ስኮሊኦስስ እና ኪፎሊሲስ ይባል በጀርባ አጥንት ወይም ህብለ ሰረሰር ላይ የሚከሰት ጉብጠት ነው። የጤና ችግሩ ተመሳሳይ ይመስል እንጂ የሚሰትበት ቦታና መስንኤው የተለያየ መሆኑን የአጥንት ህክምና ከፍተኛ ባለሙያው ዶክተር ውብታየ ዱሬሳ ተክሌ ይናገራሉ። ህብለ ሰረሰር ላይ የሚከሰተው እብጠት ዕድሜ ገፍቶ የሚከሰትበት አጋጣሚ እንዳለ ሁሉ እንዲህ ሆነው የሚወለዱ ሕጻናትም እንዳሉም ነው የአጥንት ህክምና ከፍተኛ ባለሙያው የገለጹልን።

ኪፎሊሲስ እና ስኮሊኦስስ አንድ የሚያደርጋቸው በጀርባ አጥንት ላይ የሚከሰቱ ችግሮች መሆናቸውን የገለጹት አጥንት ከፍተና ህክምና ባለሙያው ብዙውን ጊዜ ኪፎሲስ በሁለት ወይም በሦስት አጥንቶች መካከል የሚፈጠር ሲሆን፤ ችግሩ ያጋጠመው ሰው አንገቱ ስብር ብሎ አጎንብሶ ለመሄድ እንደሚገደድ ነው የተናገሩት። በዚያም ላይ በሁሉም የጀርባ አጥንት አካባቢ ወደላይ ከፍ ብሎ፣ ከመካከል ወይም ዝቅ ብሎም ሊፈጠር ይችላል፤ ስኮሊኦሲስ ግን አጥንቱ ጎብጦ የተጠማዘዘ እንደሚሆን እና በተለይ ደግሞ የሚፈጠረው በሳንባ ማቀፊያ አጥንቶች አካባቢ እንደሆነ ገልጸዋል። ሙያዊ ማብራሪያ የሰጡንን የአጥንት ከፍተኛ ህክምና ባለሙያ ዶክተር ውብታየንም እናመሰግናለን።

ሙሉ ማብራሪያውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

 ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

 

 

Audios and videos on the topic