ስንዴና ተዛመተ የተባለው «ዋግ» ፣
ረቡዕ፣ ነሐሴ 30 2004ማስታወቂያ
የተዛመተ መሆኑ ሲታወቅ፤ እስከሩቅ ምሥራቅ እንዳይዛመት ሥጋት አለ። ከአርሶ አደሮችና ሳይንቲስቶች የተሰበሰበ መረጃ ይዞ የተነሣው «ረስት ትራከር» የተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት፣ በ 27 አዳጊ አገሮች፤ የስንዴን ይዞታ በመመርመር ላይ መሆኑን ጠቁሞአል።
Borlaug Global Rust Initiative (BGRI) የተባለው ድርጅት ምክትል ሊቀ-መንበር ሮኒ ኮፍማን፣ ከአዳጊ አገሮች፤ አፍጋኒስታን ፤ ባንግላዴሽ፤ ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ፣ ህንድ ፤ ኬንያ፣ ኔፖልና ፓኪስታን፤ ዋግን የሚቋቋሙ የተለያዩ የስንዴ አዝርእትን በማልማት እንደሚታገሉ ቢጠቅሱም፤ በቅርቡ ፣ ይኸው ዋግ ይበልጥ የሚያሠጋት አገር ኢትዮጵያ ናት ማለታቸው አላስደነገጠንም ማለት አይቻልም።
በመሆኑም ፤ ከቅርብ ከሚከታተሉ ኢትዮጵያውያን ጠበብት መካከል፤ በእንግሊዝኛው Ethio-Organic Seed Action የተሰኘው፣ በተለይ በግብርናው ቴክኒክ ዘርፍ ላይ የተሠማራው ፤ የመንግሥት ያልሆነው ድርጅት ዋና ኀላፊ የሆኑትን ባለሙያ፣ ዶ/ር ረጋሣ ፈይሣን ፣ አሁን የተነገረለት ስንዴን ፍሬቢስ የሚያደርገው ዋግ በአዲስ መልክ ያገረሸ ፣ ወይስ የቆየ ነው? የኢትዮጵያ የስንዴ አዝርእት ይዞታስ በምን ላይ ይገኛል በማለት ጠይቄአቸው ነበር።---
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ