ስነፍጥረት ሲመረመር | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 10.06.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ስነፍጥረት ሲመረመር

ከዋክብትን ፣ በቀን ፣ ለምን ማየት አንችልም? ሰማዩ ፣ ለምን ሰማያዊ ቀለም ሊኖረው ቻለ? በኅዋ፣ በሰዓት 107,200 ኪሎሜትር ከምትከንፈው ምድራችን (ፕላኔታችን) እንዴት ተሽቀንጥረን አንወድቅም? እነዚህን የመሳሰሉ አያሌ ጥያቄዎችን መደርደር ፤ መልሳቸውንም ማቅረብ ይቻላል!

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:34
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:34 ደቂቃ

ስነፍጥረት ሲመረመር

Edwin Powell Hubble የተባለው አሜሪካዊ የሥነ ፈለክ ሊቅ እ ጎ አ በ 1929 ፣ ፍጥረተ ዓለም እየሠፋ ፤ እየተለጠጠ ፣ የሚሄድ መሆኑን በምርምር እንደደረሰበት አስገነዘበ። ቁስ አካል፤ ገዝፍ ያላቸው ነገሮች፤ ኅዋና ጊዜም ቢሆን ፣ ሁሉም መነሻ እንደነበራቸው አስረዳ። በኅዋ ፣ ከሜርኩሪ እስከ ኔፕቱን 8 ቱ ፕላኔቶች ፣ ከዋክብት ፤ በአጠቃላይ ፣ ፍኖተ ሃሊብ በተሰኘው ክፍል የሚገኙ ፀሐያዊ ጭፍሮች(ጋላክሲ) አንድ ብቻ ሳይሆን አያሌ ጋላክሲዎች መኖራቸውንም በተመራመረበት የሩቁን አጉልቶ በሚያሳይ ልዬ መነጽር (ቴሌስኮፕ) ረዳትነት አረጋገጠ። ኅዋ ፣ 13,7 ቢሊዮን ዓመት ገደማ ዕድሜ አለው የተባለውም ከዚያ ምርምር ወዲህ ነው። በስማቸው የተጠራው ባለቴሌስኮፕ መንኮራኩር ፣ ወደኅዋ ዘልቆ በመግባት እስካሁን መረጃዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛል። ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic