ስነውደን፣ ሩሲያና አሜሪካ | ዓለም | DW | 02.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ስነውደን፣ ሩሲያና አሜሪካ

የዩናይትድ እስቴትስ ብሔራዊ የስለላ ድርጅት አባል የነበረውና ፤ ከ2 ወራት ገደማ በፊት ከድቶ፤ ምሥጢሮችን በማጋለጥ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመነጋገሪያ አጀንዳ ያስከፈተው ኤድዋርድ ስነውደን ፤ ትናንት ሩሲያ ውስጥ ለአንድ ዓመት ጊዜያዊ ተገን ማግኘቱ ፤

በሩሲያ፤ በዩናይትድ እስቴትስና በ 3ኛ ወገኞችም አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው።  የሩሲያ ተገን መስጠት በሁለቱ ኀያላን መንግሥታት  ግንኙነት ላይ የሚያስከትለው ሳንክ እስከምን ድረስ ይሆን? ሩሲያ ፣ ለስነውደን  ለአንድ ዓመት ተገን መስጠቷን ትናንት ይፋ ካደረገች ወዲህ፣ በመጪው መስከረም ፤ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ የቡድን 20 አባል ሃገራት  ስብሰባ ፣ ከመካሄዱ በፊት ጥቂት ቀደም ብለው  ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር  ተገናኝተው ይነጋገራሉ? አይነጋገሩም ? አሁን የተሰጠ ምላሽ የለም። 

ሁለቱን መንግሥታትና ሌሎችንም ያነካካ ጣጣ አመጣ የሚባለው  ኤድዋርድ ስነውደን፣ ተገን አግኝቶ ከሞስኮ ከአኤሮፕላን ማረፊ ጣቢያ መውጣቱንና አሁንም በአደባባይ እንደማይታይ የገለጡት ጠበቃው፣ አናቶሊ ኩቸሬና ናቸው።

«የሚኖርበትን ቦታ በተመለከተ፣ ራሱ ነው የሚመርጠው። በሆቴል  በአንድ »አፓርትመንት» ወይም አንድ ቤት በመከራየት --ምርጫው የራሱ ነው። በዓለም ውስጥ እጅግ ከሚፈለጉት ሰዎች መካከል አንዱ እንደመሆኑ መጠን፤ የሚኖርበት ቦታ ፍጹም አስተማማኝ እንዲሆን ማድረጉ የማይቀር ነው።»

ሩሲያ ለኤድዋርድ ስነውደን ተገን የሰጠች ፤ አሜሪካዊው ወታደር ብራድሊ ማኒንግ፤ በአሜሪካ ላይ የስለ ተግባር ፈጽሟል የአሜሪካን ምሥጢራትም ለ «ዊኪሊክስ» አሳልፎ ሰጥቷል ተብሎ ብይን ባገኘ በ ሁለተኛው ቀን ነው።

የስነውደን ጠበቃ ኩቸሬና እንዳብራሩት ከሆነ፤ ይዋል ይደር እንጂ ስንውደን ፤ ከህዝብ ጋር መገናኘቱና ለመገናኛ ብዙኀንም ቃለ ምልልስ መስጠቱ የማይቀር ነው። አሁን ግን እንግዳ በሆነበት አገር ለመኖር የሚያስፈለገው ትምህርት ይሰጠዋል። ስነውደን ፤ ተገን በማግኘቱ ሩሲያን ከማመሥገኑም፤ የዩናይትድ እስቴትስን መንግሥት፤ ለዓለም አቀፍም ሆነ ለሀገራዊ ህግ «አክብሮት» የሌለው ነው በማለት መውቀሱ  ወስቷል።

በዩናይትድ እስቴትስ ፣ ኤድዋርድ ስነውደን ፣ በስላለና ብሔራዊ የስለላ ድርጅቱ የሌሎችን ምሥጢር እንዴት እንደሚያዳምጥ ፣ የአሠራሩን ዘዴ የሚያሳየውን  ሰነድ ፣ በመሥረቅ  ይፋ ያጋለጠ ሲሆን ፤ በእነዚህ  ጉዳዮች እንዲያዝ ትእዛዝ የተላለፈበት ሰው ነው።

የኋይት ሐውስ ቃል አቀባይ፤ ጄይ ካርኒ ------

«እስነውደን፣ ወደ ዩናይትድ እስቴትስ ተገዶ እንዲመለስና   በቀረበበት ክስ ሳቢያ ከህግ ፊት እንዲቀርብ፣ በግልጽ ፤ በአደባባይ ብንጠይቅም፣ የሩሲያ መንግሥት እዚህ ውሳኔ ላይ በመድረሱ ፣ በጣም ነው ያናደደን።»

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን፤ ስነውደን ፤ለአንድ ዓመት  ጊዜያዊ ተገን ስላገኘበት ሁኔታ ገና አስተያየት አልሰጡም። ምናልባት ፣በበጋ ወቅት ወጣቶች  በሚደረጉት ሰብሰባና በሚሰጡት ድጋፍ ፤ ዛሬ በዚያ ተገኝተው  በሚያሰሙት ንግግር ላይ ሊያወሱ ይችላሉ ተብሎ ይታሰባል።

የዩናይትድ እስቴትስና የሩሲያ ግንኙነት በስነውደን ምክንያት ይበልጥ ሊሻክር ይችላል የሚል አስተያየት  በተለይ ከዩናይትድ እስቴትስ በኩል ጠንከር ብሎ ሲሰማ፣ ከሩሲያ በኩል ደግሞ ፤ ያን ያህል ከቆየ ማለፊያ ግንኙነት በበለጠ ሁኔታ መታየት የማይገባው ነው

የሚል አስተያየት ነው የሚሰነዘረው።

የሩሲያ የተለያዩ ፖለቲከኞች የሆነው ሆኖ መንግሥታቸው ለስነውደን ተገን መስጠቱን አመሥግነዋል። የገዢው የተባበረችው ሩሲያ ፓርቲ አባልና የፓርላማ አባል ቪያቼስላቭ ኒኮኖቭ፣ ለስነውደን ተገን ባንሰጥ ኖሮ ፤ ህዝብ ፤ ሩሲያን ኀያል መንግሥት ናት ብሎ ማመኑን ፣ ያቆም ነበር ነው ያሉት።

ስነውደን ወደ ቦሊቪያ፣ ኒካራጉዋም ሆነ ቬነዝዌላ መጓዝ ይችላል፤ የፖለቲካ ተገን ሊሰጡት ቃል ገብተዋልና!ይሁንና የስነውድን ታማኝ  መሆኑ የሚነገርለት ጋዜጠኛ   Glen Greenwald ፤ ስነውደን ሌላውን አማራጭ  የሚቀበል መሆኑ አጠራጣሪ ነው ይላል።

«ላቲን አሜሪካ ፣ በመልክዓ-ምድር  አቀማመጥ ብቻ ሳይሆን ፣ በብዙ ጉዳዮች ፣ እጅግ ፈንጠር ያለ በመሆኑ፤ አሁን እንደሚመስለኝ፣ ትኩረቱ ፣ ሩሲያ ውስጥ ደህንነቱን መጠበቅ ነው።»

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic