«ስታፍን ዴ ሚስቱራ» በተመድ ለሶርያ የሰላም መልክተኛ | ዓለም | DW | 01.02.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

«ስታፍን ዴ ሚስቱራ» በተመድ ለሶርያ የሰላም መልክተኛ

ሶርያ ሰላምን እንድታገኝ የሚመኙት በእርስ በርስ በርሶ ጦርነት ዉስጥ የተዘፈቁት ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በጦርነቱ ከሃገሪቱ በገፍ የተሰደዱትና ወደ ሶርያ መመለስ የሚፈልጉትም ዜጎች ናቸዉ። እንድያም ሆኖ በሶርያ የሚገኙትን ተቀናቃኝ ወገኖች ለሰላም ድርድር ወደ ክብ ጠረቤዛ ማምጣት በራሱ፤ ከባድ መልስ ያላገኘ አስቸጋሪ ሥራ ሆኖ ቆይቶአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:28

በተመድ ለሶርያ የሰላም መልክተኛ


በመንግሥታቱ ድርጅት 40 ዓመታት በስኬታማ የዴፕሎማሲ አገልግሎታቸዉ የሚታወቁት ትዉልደ ስዊድን ኢጣልያዊዉ የተመድ የሶርያ የሰላም ልዩ መልክተኛ ስታፍን ዴ ሚስቱራ፤ በሶርያ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማስገኘት ምንም አይነት መሰናክል ያንበረከካቸዉ አይመስልም።


የሰላም መልክተኛ በመሆን በተመድ ከአራት አስርተ ዓመታት በላይ ያገለገሉት የኢጣልያ ዜግነት ያላቸዉ ትዉልደ ስዊድናዊዉ ስታፍን ዴ ሚስቱራ አልጀርያዊዉ ላክዳር ብራሂሚ ያቋረጡትን የሶርያ ተልዕኮ እንዲረከቡ ከመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ የስልክ ጥሪ የደረሳቸዉ በጎርጎረሳዉያኑ 2014 ነሐሴ ወር ላይ ነበር።
በተፈጥሮዩ ተስፈኛ ነኝ የሚሉት ስታፍን ዴ ሚስቱራ ከመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ጊሙን ይህ የስልክ ጥሪ ሲደርሳቸዉ የ68 ዓመት እድሜ ባለፀጋ ነበሩ። የባልካን ሃገራትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ሶማልያ፤ ኤርትራ እንዲሁም በሌሎች ዓለም ሃገራት ለ 42 ዓመታት ከፍተኛ ፖለቲካዊ ዉዝግብ፤ ጦርነት ረሃብ በሚታይበት ቦታ ሁሉ በዲፕሎማስያዊ ተግባር ይገኙ የነበሩት ስታፋን ደ ሚስቱራ 19 የዉጭ ሃገራት ተልኮዎችን ተከታትለዋል። የኢራቅ ከዝያም የአፍጋኒስታን ልዩ የተመድ መልዕክተኛ ሆነዉም አገልግለዋል።
ቆየት ብሎ በጎርረሳዉያኑ 2014 ዓ,ም ነሐሴ የተመድ ዋና ፀሃፊ ባን ጊሙን ስታፋን ዴ ሚስቱራን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲረድዋቸዉ ተማፀኑዋቸዉ። ተማጽኖዉ አምስት ዓመት ግድም የሆነዉ በደም አፋሳሹ የሶርያ የርስ በርስ ጦርነትና ግድያ፤ ሞት፤ እንድያስቆሙ የሚል ነበር።
ዴ ሚስቱራ በዚህ ተልዕኮዋቸዉ በዓለም ኃያላኑ ሃገራት ሩስያና ዩኤስ አሜሪካ፤ እንዲሁም በሶርያ አካባቢ ሃገራት በሳዉዲ አረብያና በኢራን መንግሥታት ብሎም በሶርያ ዉስጥ በሚገኙ ተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል የሰላም መሪያቸዉን መዘወር ይኖርባቸዋል።
«ይህ በቃ ማለት በቃ ነዉ የሚለዉ ስሜት»
በስታፋን ዴ ሚስቱራ ሕይወት ይህ «ይበቃል»

የሚለዉ ስሜት ሲከሰት ለመጀመርያ ጊዜ አልነበረም። ዴ ሚስቱራ በካቡል አፍጋኒስታን አንድ የንግድ የአየር መንገድ በነፃ ምግብን እንዲያመላልስ እሺ አሰኝተዋል። በስርየቮ በወታደር ተከባ የምትገኝ ከተማ ሰዎች የሕክምና መድኃኒትና ምግብ ደብቀዉ እንዲያስገቡ ከፍተኛ ሚናን ተጫዉተዋል። በሱዳን የሰላም ድርድር ስኬት ባጣ ጊዜ፤ ግመሎችን ተከራይተዉ መኪና በማይደርስባቸዉ ገጠራማ አካባቢዎች የክትባት መድኃኒት እንዲደርስ ትልቅ ስራን ሰርተዋል። ስታፋን ደ ሚስቱራ እስካሁን ባከናወኑዋቸዉ ተግባሮች ሁሉ የመንግሥታቱ ድርጅት ስኬት ሊያገኝ የማይችል ከባድ ብሎ የሰየማቸዉን ነገሮች ነዉ።
« ስኬት ሊያገኝ የማይችል ከባድ የተባለዉን ነገር ታስታዉሳላችሁ። በርግጥ ምናልባት የሶርያ ጉዳይ የሚሳካ ተልዕኮ ይሆናል።»
ዴ ሚስቱራ በዴፕሎማስያዉ ሥራቸዉ ሁሌም ቢሆን ተስፋን የሰነቁ መሆናቸዉ ተዘግቦላቸዋል። የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን የድርጅቱ የሶርያ ልዩ መልክተኛ ብለዉ ሲሾሙዋቸዉ፤ በሶርያዉ ጦርነት አማፅያን፤ የፕሬዚዳን አሳድ መንግሥት፤ ጽንፈኛዉ «እስላማዊ መንግሥት» እና ሌሎች ቡድናት በጦርነቱ እናሸንፋለን ሲሉ ፤ተስፋ በሰነቁበት ፖለቲካዊ መፍትሄን ለማምጣት ነዉ። ከዚህ ቀደም አልጀርያዊዉ ላክዳር ብራሂሚና የቀድሞዉ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን በመንግሥታቱ ድርጅት የሶርያ ልዩ መልክተኛ ሆነዉ ከፍተኛ ጥረቶችን አድርገዋል። እንደ ሚስቱራ፣
«የጦር መሳርያ መልስ አይሆንም፤ ሰላምን ለማስገኘት መፍትሄዉ ዉይይት ብቻ ነዉ።»
ዴ ሚስቱራ በሶርያ ፖለቲካዊ መፍትሄን ለማስገኘት ይፋዊና ይፋዊ ባልሆነ መልኩ የጀመሩት ድርድርና ዉይይት ከወር ወር ቀጥሎአል።

በርግጥ እስከ አሁን በቁጥር ስንት የሶርያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማነጋገራቸዉን እንኳ በዉል አያዉቁም። በሶርያ የሚገኙት የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከብዛታቸዉ የተነሳ ለሰላም ድርድሩ እንኳ በአንድ ጠረቤዛ በአንድ ሰፊ ክፍል ለመሰባሰብ በቂ ቦታን አያገኙም። እንደ ዴ ሚስቱራ እስከዛሬ 18 የሶርያ ቡድኖችን ማነጋገራቸዉን ገልፀዋል።
ሰባት የተለያዩ የዓለም ቋንቋዎችን የሚናገሩት ዴ ሚስቱራ በሶርያ የሚገኙ ነዋሪዎች ሃገራችን እጅግ ተጎድታለች። ተሰቃይታለች በቃ ያሉበት ጊዜ መሆኑን ይናገራሉ። ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በኋላ አባታቸዉ ዜግነት አልባ ስደተኛ እንደነበሩ የሚናገሩት ዴ ሚስቱራ በዝያን ጊዜ የ 10 ዓመት ልጅ ሳሉ ዜግነት አልባ ስደተኛ ሆኖ ሰብዓዊ ክብርን ማጣት ምን ማለት እንደሆን ያወቁት የዝያን ጊዜ እንደሆነ ገልፀዋል። የሶርያዉ ተልዕኮ ስኬት አልባ ይሆን? በሶርያ ፖለቲካዊ መፍትሄ ይመጣል ብለዉ ተስፋን የሰነቁትና ተልዕኮዋቸዉንን የጀመሩት ዴ ሚስቱራ ይህ አይነቱ ጥርጣሪ ባይሆን ለመጀመርያ ወቅት አሁን ከአዕምሮዋቸዉ እንደፋቁት ነዉ የተዘገበዉ።


ጊዮርግ ሽቫርተ / አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic