1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስራ ፈላጊ እና አሰሪ ያገናኘው መድረክ

ዓርብ፣ ሰኔ 28 2016

የአፍሪቃ ልማት ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው አፍሪቃ ካላት ከ420 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ውስጥ ከሶስት አንዱ ስራ አጥ ናቸው። ባንኩ በቀጣዩ የጎርጎርሳዉያን 2025 የስራ አጦቹን ቁጥር ከ263 ሚሊዮን በላይ ያደርሰዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ተደራራቢ ግጭት እና ጦርነት ውስጥ ላሉ ሃገራት አሃዙ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ የተቀመጠ መረጃ የለም።

https://p.dw.com/p/4huiG
Teilnehmer des Arbeitnehmer-Arbeitgeber-Forums, Hawassa, Äthiopien
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ለስራ ፈላጊ ተመራቂ ወጣቶች ተስፋ የፈነጠቀው መድረክ

 

ስለ ስራ አጥነት ሲነሳ በማደግ ላይ ያሉ የሶስተኛ ዓለም ሃገራት በዋነናነት የችግሩ ሰለባ ሲሆኑ ይታያል። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አፍሪቃ በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች። አፍሪቃ ካላት የስራ አጥ ቁጥር ውስጥ ወደ 60 ከመቶ ገደማ የሚሆኑት ወጣቶች ስለመሆናቸው መረጃዎች ያሳያሉ ። ኢትዮጵያም እንደተቀሩቱ የአ,ፍሪቃ ሀገራት ሁሉ የስራ አጥነት የተንሰራፋባት ሀገር ስለመሆኗ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ተመርቀው ስራ አጥ የሆኑ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወጣቶች ማሳያ ናቸው ።

 በሀገሪቱ ጦርነት እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ያስከተሏቸው አለመረጋጋቶች በኤኮኖሚው ላይ ያስከተለው ውድቀት መንግስት በተለመደው መንገድ ተመራቂ ተማሪዎችን መቅጠር እስኪያቅተው አድርሶታል። ቢኖርም በርካቶች እንደሚሉት ሙሰኝነት እና ዝምድና ብቃቱ እና ዝግጁነት ያላቸውን ተመራቂዎች ከስራ ጋር እንዳይገኛኑ እንቅፋት ስለመሆናቸው ነው። እንደዚያም ሆኖ ግን ከሰሞኑ ከወደ ሓዋሳ የተሰማው መረጃ  ለብዙሃኑ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ሳይሆን እንዳልቀረ ነው። መድረኩ የግልም ሆነ ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሰራተኛ ቅጥር ፍላጎታቸውን በቀጥታ ሊያሳኩ የሚችሉበት ስራ አጡ ወጣትም በቀጥታ ከቀጣሪዎቹ ጋር ፊትለፊት ተገኛኝቶ የሚደራደርበት የስራ እና አሰሪ መገናኛ ወይም የስራ ገበያ መከፈቱ ተገልጿል።

በእጅ ከያዙት ይልቅ ተስፋ የሚያደርጉበት ይበልጣል
የአፍሪቃ ልማት ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው አፍሪቃ ካላት ከ420 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ውስጥ ከሶስት አንዱ ስራ አጥ ናቸው። ይህ ቁጥር በዚህ አያበቃም የሚለው ባንኩ በቀጣዩ የጎርጎርሳዉያን 2025 የስራ አጥ ወጣቶችን ቁጥር ከ263 ሚሊዮን  በላይ ያደርሰዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ተደራራቢ ግጭት እና ጦርነት ውስጥ ላሉ ሃገራት አሃዙ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ የተቀመጠ መረጃ ባይኖርም በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ስራ አጥ ስለመሆናቸው መግለጽ አያዳግትም።

ስራ ለማግኘት አንድም በጉቦ አልያም ዘመድ ሊኖር ይገባል ይላሉ ከሰሞኑ በሃዋሳ ስራ እና ሰራተኛን ለማገናኘት በተከፈተ አንድ መድረክ ላይ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ። መድረኩ ከዚህ ቀደም በተለየ ሁኔታ ስራ ፈላጊ ተመራቂ እና ቀጣሪን ፊት ለፊት ያገናኘ ነው ተብሎለታል። 
«ስሜ ሲሳይ አራጋው ይባላል። የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ ተማሪ ነኝ ። ዘንድሮ  እንደእግዚአብሔር ፈቃድ ተመራቂ ተማሪ ነኝ። አሁን እዚህ የተገኘሁት ደረጃ ዶት ኮም  ከማስተር ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ቀጣሪ ድርጅቶችን ወደ ጊቢ በማምጣት ስራ ፈላጊ ተማሪዎችን ደግሞ ከእነርሱ ጋር የማገናኘት ስራ ሰርቶ እናን ደግሞ ኑ ወደ ሚመለከታችሁ ሲቪያችሁን አስገቡ ብሎ ጠርቶን ነው የመጣነው»

ሲሳይ አራጋው የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ ተማሪ
ስራ ለማግኘት አንድም በጉቦ አልያም ዘመድ ሊኖር ይገባል ይላሉ ከሰሞኑ በሃዋሳ ስራ እና ሰራተኛን ለማገናኘት በተከፈተ አንድ መድረክ ላይ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ። መድረኩ ከዚህ ቀደም በተለየ ሁኔታ ስራ ፈላጊ ተመራቂ እና ቀጣሪን ፊት ለፊት ያገናኘ ነው ተብሎለታል።ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

 የሥራ እድል ፈጠራ በኢትዮጵያ 


በእርግጥ ነው እንኳንስ ተምሮ ገና ያልተመረቀ ተማሪ ይቅር እና ተመርቆ ከስራ ሳይገናኝ ዓመታትን ያሳለፈ ስንቱ እንደሆነ ቤቱ ይቁጠረው ። በገበያ ላይ ያለውን ስራ ፈላጊ ወጣት ሞያተኛ መች በአግባቡ የስራ ዕድል አመቻቸንና  ተመራቂ ተማሪን ከቀጣሪ ለማገናኘት አስፈለገ የሚለው ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን እንዲህ አይነት መድረኮች ተመርቄ ስራ አገኝ ይሆን ብለው ለሚጠብቁ ተመራቂዎች አዲስ ተስፋ ይዞ ስለመምጣቱ ነው ሲሳይ የሚናገረው። 
« በተለይ በተማሪ በኩል ስናይ ይህ ለእና በጣም ጠቃሚ ዝግጅት ነው ፤ ምክንያቱም አሁን ስራ በዘመድ፣ በጉቦ ሆኗልና እዚህ ቦታ ደግሞ ምንም አይነት የገንዘብ እና የሰው ንክኪ የማይታይበት ነው ስራ ፈላጊው እና ቀጣሪው በቀጥታ የሚገናኙበት ነው »   
ዳግማዊት ተካልኝም እንደ ሲሳይ ሁሉ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሎጀስቲክስ ኤንድ ሰፕላይ ቼንጅ ተመራቂ ተማሪ ናት ፤ ስራ እና ሰራተኛን ለማገናኘት የተዘጋጀው መድረክ ሁሉም እንደመሻቱ ሊገናኝ ዕድል የሚፈጥር ነው ባይ ናት ።
« እዚህ የተገኘሁት ያው የስራ ዕድሉን ለመጠቀም ነው። እና በተዘጋጀልን የስራ ዕድል መጀመሪያ ስልጠና ወስደን በዚያ መሰረተe በተዘጋጀልን ብዙ የስራ አማራጮች ላይ ለማመልከት ነው። እንደተመራቂ ተማሪ ደግሞ ይህ በጣም ትልቅ ዕድል ነው። » 

የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎቹን የሚያባንኗቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች 

ወጣቶች እና የስራ ዕድል ሲነሳ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የአፍሪቃ ሃገራት ለፍልሰት እየተዳረጉ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ። በሀገር ውስጥ በተማሩበት የትምህርት እና የሞያ መስክ የስራ ዕድል በማጣታቸው ብቻ የስራ ዕድል ይገኝበታል ወደሚሉበት የዓለም ክፍል መሰ,ደድ ዕጣ  ፈንታቸው ይሆናል። ለዚያውም ከእርስ በእርሱ ግጭት ጦርነት ከተረፉ ። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን አሁን ለዓመታት ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚፈስባቸው ህክምና እና ምህንድስናን ጨምሮ በበርካታ የስራ መስኮች የስራ ዕድሉ  እየጠበበ እና ውድድሩም በዚያው ልክ እያየለ ስለመሄዱ ይነገራል። እንደዚያም ሆኖ ግን ጠባብም ሆኖ ባለው የስራ ዕድል የአሰሪ እና ሰራተኛ እንደፈለጉ አለመገናኘት በስራው ምርታማነት ላይ ጥያቄ ሲያስነሳም ይሰማል። 
በሀዋሳው የአሰሪ እና ሰራተኛ መገናኛ መድረክ ላይ የተገኙት  የአብርሽ እና ቤተሰቡ የቆዳ ውጤቶች  አምራች ኢንዱስትሪ ምክትል ስራ አስኪያጅ እንዳሉት የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መድረክ አዲስ የስራ እና ሰራተኛ መገናኛ መድረክ የፈጠረ ነው ። 
«መድረኩ በጣም የሚገርም እና ኢትዮጵያ ከተለመደው የሰራተኛ እና አሰሪ ከሚገናኙበት ስረዓት ለየት ያለ እና በተሻለ ሁኔታ የሚገናኙበት መድረክ ነበር ። በጣም ብዙ ዓመት የተማሩ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች ከድርጅቶች ጋር የሚገናኙበት ዕድል ነበር ። እኛም የተለያዩ ሰራተኞችን መልምለን ለመቅጠር ዝግጅት ላይ ነው ያለነው። በቂ ስልጠና ያገኙ ሞያተኞችን ስለምናገኝ ለእኛ ጥሩ ዕድል ነው»

ወጣት መሳይ አየለ
በሀዋሳው የአሰሪ እና ሰራተኛ መገናኛ መድረክ ላይ የተገኙት  የአብርሽ እና ቤተሰቡ የቆዳ ውጤቶች  አምራች ኢንዱስትሪ ምክትል ስራ አስኪያጅ እንዳሉት የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መድረክ አዲስ የስራ እና ሰራተኛ መገናኛ መድረክ የፈጠረ ነው ።ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

 ባልተለመደ አካባቢ ሞዴልነትን እያስተዋወቀ ያለው ወጣት


ሲያም አየለ የአፍሪካ ጆብ ኔትወርክስ የኢትዮጵያ ስራአስኪያጅ ናት ። ድርጅቱ ከሓዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በየዓመቱ በትብብር የሚሰጠው ተመራቂዎችን ለስራ የማዘጋጀት መርኃ ግብር በዚህ ረገድ የሚፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት አጋዥ መሆኑን ትናገራለች። 
ስለስራ አጥነት ሲነሳ በተለይ ወጣቱ ምን ያህል ችግር ውስጥ እንዳለ ለማወቅ በእርግጥ ጥናት እና ምርምር ማድረግ አይጠበቅም። በሀገሪቱ አቅም ያለውን የስራ ዕድል እና በየዓመቱ ከየዩኒቨርሲቲው ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶችን ማመሳከሩ ብቻውን በቂ ነው። ተመራቂዎች የስራ ዕድል እንዲያገኙ በየዩኒቨርሲቲው የሚደረጉ የቅድመ ስራ ስለጠናን ጨምሮ ስራ እና ሰራተኛን ለማገናኘት የሚደረጉ ጥረቶች ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን አሁንም በርካታ የስራ ዕድል ያለህ እያሉ በየሰፈሩ የሚንከራተቱ ወጣቶች አሉ ።በውጭ አገር ላሉ ወጣት አፍሪቃውያን በሀገራቸው መዋለ ንዋይ ማፍሰስ ቀላል ነውን?

ሲያም አየለ የአፍሪካ ጆብ ኔትወርክስ የኢትዮጵያ ስራአስኪያጅ
ስለስራ አጥነት ሲነሳ በተለይ ወጣቱ ምን ያህል ችግር ውስጥ እንዳለ ለማወቅ በእርግጥ ጥናት እና ምርምር ማድረግ አይጠበቅም። በሀገሪቱ አቅም ያለውን የስራ ዕድል እና በየዓመቱ ከየዩኒቨርሲቲው ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶችን ማመሳከሩ ብቻውን በቂ ነው።ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

በእርግጥ ለሁሉም በአንድ ጀንበር የሚመጣ በረከት ላይኖር ይችላል ፤ ይህን የትኛውም ሀገር አላሳካውም ። ቢሆንም ግን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ያለችውን ትንሽዬ የስራ ዕድል ምን ያህል በፍትሃዊነት ለወጣቱ እየተዳረሰ ነው የሚለው ሊጠየቅ የግድ ይላል። እንደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያሉቱ ደግሞ ተማሪዎቻቸውን ንድፈሃሳብ ብቻ አስተምረው አስመርቀው መሸኘት ብቻ ሳይሆን እዚያው እነርሱጋ እያሉ ተጨማሪ ስልጠና አግኝተው ራሳቸውን ለስራ አዘጋጅተው እና ከአሰሪ ጋር የሚገናኙባቸውን መድረኮች መፍጠሩ ፤ ያሳደጉትን ለፍሬ መብቃቱን ቆመው የማየት ያህል ነውና ይበል ያሰኛል። 
ታምራት ዲንሳ 
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር