«ስማርት» መታወቂያ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 06.11.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

«ስማርት» መታወቂያ

«ስማርት አይዲ» የተባለዉ ማንነትን መለያ መተግበርያ ወይም application የዜጎችን ዝርዝር መረጃዎች የሚይዝ፣ የወረቀት አሰራርን የሚያስቀር እና  ሕገ ወጥ መረጃን ለመለየት የሚያስችል ነው፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 08:50

የኤሌክትሮኒክስ መታወቂያ መተግበሪያ

የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመታወቂያ ደብተርን የሚተካ ሶፍትዌር በቅርቡ አዘጋጀተዋል።«ስማርት አይዲ» የተባለዉ ማንነትን መለያ መተግበርያ ወይም application የዜጎችን ዝርዝር መረጃዎች የሚይዝ፣ የወረቀት አሰራርን የሚያስቀር እና  ሕገ ወጥ መረጃን ለመለየት የሚያስችል ነው፡፡አበልፃጊዎቹ የመቀሌ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የ2011 ዓ.ም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቃን የሆኑት ኪዳነ ገብረመድህን፣ አረጋዊ ሀይለየሱስና ሌሎች ባልደረቦቻቸው ሲሆኑ ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት አልመው እንደሰሩት ተናግረዋል፡፡ሶፍትዌሩ በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የሚሰራ መሆኑም አበልፃጊዎቹ ይናገራሉ።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ በዛሬዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዝግጅታችን አዲሱን ቴክኖሎጂና አበልፃጊዎቹን ያስተዋዉቀናል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

 


 

Audios and videos on the topic