ስለ እስረኞች ፍቺ የተቃዋሚዎች መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 16.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ስለ እስረኞች ፍቺ የተቃዋሚዎች መግለጫ

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ትላንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ  528 ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንደሚፈቱ ተናግረዋል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ 115ቱ ጉዳያቸው በፌደራል ደረጃ የተያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተፈቺዎቹ ዝርዝር ባይገለጽም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጉዳዩን አስመልክቶ አቋማቸውን ዛሬ ይፋ አድርገዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:36

የተፈቺ እስረኞች ቁጥር በቂ አይደለም- ተቃዋሚዎች

በእስረኞች ፍቺ ላይ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ናቸው፡፡ ድርጅቶቹ በመግለጫቸው ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ እስረኞች እንዳሉ ማመኑን እና ለመፍታት ቃል መግባቱ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም አገዛዙ ሊታመን የሚችለው የገባውን ቃል ተግባራዊ ሲያደርግ ብቻ ነው ብለዋል፡፡ 

የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃል “ማታ እንደሰማነው በተለይ ክልል ላይ በርካታ ሰዎችን መፍታቱን ነግሮናል፡፡ ከዚያ ውጭ በፌደራል ላይ 115 ያህሉ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ ይፈታሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን እኛ እያልን ያለነው ይሄ በፍጹም በቂ አይደለም፡፡ እስር ቤት ውስጥ 30 ሺህ እና 40 ሺህ እስረኛ ባለበት እና በተለይም ጎምቱ የተባሉ ፖለቲከኞች በአርበኞች ግንቦት 7፣ በኦነግ፣ በኦብነግ ስም ታፔላ የተለጠፋባቸው የታሰሩ በርካታ ዜጎች ስላሉ እነርሱ የሚፈቱበት መልኩ ማርፈድም የለበትም፤ ጊዜ ሊወስደም አይገባም” ብለዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ 

 

Audios and videos on the topic