« ስለ ኢትዮጵያ » የሙዚቃ አልበም በአዲስ ዓመት | ባህል | DW | 12.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

« ስለ ኢትዮጵያ » የሙዚቃ አልበም በአዲስ ዓመት

አንጋፋ እና ወጣት ድምጻውያንን ጨምሮ በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት እና በአንድ የሙዚቃ አልበው ውስጥ በርካታ ዘፈኖችን በማካተት የመጀመርያው ሳይሆን በተነገረለት ስለ «ስለ ኢትዮጵያ » አልበም የሀገር ፍቅር ስሜት ፣ የሰላም እና መረጋጋት ምኞት እንዲሁም ዕድገት  እና ብልጽግናን የሚመኙ ዜማዎች እንደተካተቱበት አዘጋጆቹ ይናገራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:42

«ስለ ኢትዮጵያ » አዲስ የሙዚቃ አልበም ተመረቀ

ጤና ይስጥልን አድማቾቻችን በድጋሚ እንኳን ለ2014 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያልን የአዲሱን ዓመት የመጀመርያውን የመዝናኛ ዝግጅታችንን ይዘን ቀርበናል እስከ ዝግጅቱ ፍጻሜ አብራችሁን እንድትቆዩ የአክብሮት ግብዛችን ነው። 
አሮጌው ዓመት አልፎ በአዲስ ሲተካ በተለይ አዳዲስ የአውደ ዓመት የሙዚቃ ስራዎችን ጨምሮ በርካታ ነጠላም ሆነ የተሟሉ የሙዚቃ አልበሞች ተጠናቀው ለአድማጭ ተመልካቹ ይቀርባሉ ። በዛሬው የመዝናኛ ዝግጅታችን በአይነቱ ለየት ብሎ ከ100 በላይ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት እና ባለፈው ሐሙስ ጳጉሜ 04 ቀን 2013 ዓ/ም በብሔራዊ ቤተ መንግስት በተመረቀው   « ስለ ኢትዮጵያ » በተሰኘው የሙዚቃ አልበም ላይ ትኩረቱን አድርጓል።
አንጋፋ እና ወጣት ድምጻውያንን ጨምሮ በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት እና በአንድ የሙዚቃ አልበው ውስጥ ምናልባትም በርካታ ዘፈኖችን በማካተት የመጀመርያው ሳይሆን በተነገረለት ስለ «ስለ ኢትዮጵያ » አልበም የሀገር ፍቅር ስሜት ፣ የሰላም እና መረጋጋት ምኞት እንዲሁም ዕድገት  እና ብልጽግናን የሚመኙ ዜማዎች እንደተካተቱበት አዘጋጆቹ ይናገራሉ።  አቶ ልዑል ሞገስ አዲስ የተዘጋጀው የ«ስለ ኢትዮጵያ » የሙዚቃ አልበም ስራ አስኪያጅ ናቸው ። አዲሱ የሙዚቃ አልበም እንዲህ በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎችን በማሳተፍ እንዴት ሊሰራ ቻለ ? ከዶይቼቬለ የቀረበላቸው ጥያቄ ነበር። 
በሙዚቃ ስራው ላይ ከተሳተፉ አንጋፋ ድምጻውያን መካከል ድምጻዊ ጸደንያ ገብረማርቆስ አንዷ ናት። ጸደንያ በሙዚቃ ስራው ላይ እንድትሳተፍ ጥያቄ ሲቀርብላት በደስታ እንደተቀበለች ትናገራለች። እስከ ዛሬ በበርካታ ሀገራዊ የሙዚቃ ስራዎች ላይ እንደተሳተፈች የምትገልጸው ጸደንያ ይኼኛው የጋራ የሙዚቃ ስራ ግን በተሳታፊዎች ብዛት ለየት ይላል ባይ ናት ። 
ድምጻውያኑ በሙዚቃ ስራው ምን ምን ሃሳባቸውን ገለጹበት ለሚለው ጸደንያ መልስ አላት። 
በሙዚቃ ስራው በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አንጋፋው ድምጻዊ አለማየሁ እሸቴን ጨምሮ በአማርኛ እና  በተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ቋንቋዎች በማቀንቀን የሚታወቁ ድምጻውያን ተሳታፊ እንደሆኑበት ተነግሯል። ከእነዚህ ውስጥ በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ በማቀንቀን የሚታወቀው ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ ይገኝበታል።  ለሀገራዊ ጉዳይ መሰባሰብ እንደሚያስደስተው የሚገልጸው አቡሽ ስለ አባይ የተዜመውን ጨምሮ በአልበሙ ውስጥ ከተካተቱ 28 የሙዚቃ ስራዎች ውስጥ ሁለት ዜማዎችን ማበርከቱን ይገልጻል ። ወደ ስብስቡም በራሱ ፈቃድ መግባቱን ተናግሯል። 
አትፈርስም ሀገሬ እኔ እያለሁ እያለ በአፋን ኦሮሞ ባቀነቀነበት ዜማው ለሀገሩ ያለውን ፍቅር እንደገለጸ የሚናገረው አቡሽ ፤ በሙዚቃው ስሜቱን በአግባቡ እንደገለጸ ይናገራል። 
እንግዲህ አድማጮቻችን በአዲሱ ዓመር በአዲሱ «ስለ ኢትዮጵያ አልበም » የሙዚቃ ስራ ላይ ያተኮረው የዕለቱ የመዝናኛ ዝግጅታችን በዚሁ ተቋችቷል፤ ለአብሮነታችሁ ምስጋናችን ከልብ ነው ጤና ይስጥልኝ ።
ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic