ስለ አቶ አንዳርጋቸው የብሪታንያ መንግሥት ጥያቄ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ስለ አቶ አንዳርጋቸው የብሪታንያ መንግሥት ጥያቄ

አዲስ አበባ የሚገኘው የብሪታንያ ኤምባሲ ሰራተኞች የመን ካለፉት ስድስት ሳምንታት በፊት ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፋ የሰጠቻቸው እና በእስር የሚገኙትን የግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ

ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመጎብኘት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ መቅረቱ ተገለጸ። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ፣ ወኪላችን ድልነሳው ጌታነህ የላከልን ዘገባ እንዳስታወቀው፣ በብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ክፍል ኃላፊ ሚስተር ማርክ ሲሞንድስ ከትናንት በስቲያ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር አቶ ደመቀ አጥናፉን በጽሕፈት ቤታቸው አስጠርተው አነጋግረዋል።

ድልነሳው ጌታነህ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic