ስለዝግመታዊ ለውጥ፣ ሳይንሳዊና ሃይማኖታዊ አመለካከት፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 11.02.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ስለዝግመታዊ ለውጥ፣ ሳይንሳዊና ሃይማኖታዊ አመለካከት፣

ሰዎችም ሆኑ፣ በአጠቃላይ በዝች ምድር ላይ የሚገኙ፣ በአየር የሚበሩ፣ በየብስ የሚርመሰመሱና በባህር ወስጥ የሚኖሩ እንስሳትና ዐራዊት ኅልውናቸውን ለመጠበቅ በራሳቸው ላይ ያደረጉት ለውጥ ምን ይመስላል? ከውጭ ፣ የአየርና የምግብ ፣ ሌላም ዓይነት ተጽእኖ ያበረከቱት ድርሻ አለ ወይ?

default

የአሁኑ ዘመን ሰው(Homo Sapiens)ምንጭ፣ ቅድመ-ሰው፣--ከአፍሪቃ፣

ሰው፣ የመፍጠር ክህሎት ባለው ብቸኛ ኀይል፣ (እግዚአብሔር) የተገኘ፣ ወይስ በዝግመታዊ ለውጥ አሁን ከሚገኝበት የማስተዋል ደረጃ ላይ የደረሰ ፍጡር ነው? ሥነ-ፍጥረትና ሃይማኖት በምን ይስማማሉ? በምንስ ይለያያሉ?ፍጡራን፣ በዝግመታዊ ለውጥ የተገኙ መሆናቸውን በምርምር ተመረኩዞ ማብራሪያ ያቀረበው የመጀመሪያው ዕውቅ ተመራማሪ፣ ቻርለስ ዳርዊን፣ ነገ፣ የካቲት 5 ቀን 2001 ዓ ም፣ ልክ፣ 200ኛ ዓመት የልደት በዓሉ ይታሰባል። ይህን መንስዔ በማድረግ በዓለም ዙሪያ የዝካሬ ዝግጅት በመካሄድ ላይ ሲሆን እኛም ለዛሬ ስለታዋቂው እንግሊዛዊው የዝግመታዊ ለውጥ ነባቤ-ቃል ቀማሪ፣ ዳግመኛ የምንለው ይኖረናል።

T Y/SL

►◄