ስለብይኑ፣ከሀገርና ከውጭ የተሰጡ አስተያየቶች፣ | ኢትዮጵያ | DW | 13.07.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ስለብይኑ፣ከሀገርና ከውጭ የተሰጡ አስተያየቶች፣

መገናኛ ብዙኀን ፤ ዛሬ ዐቢይ ግምት ከሰጧቸው ጉዳዮች አንዱ፣ አዲስ አበባ ውስጥ በ 24 የተቃውሞ የፖለቲካ ሰዎችና ጋዜጠኞች ላይ ፍርድ ቤት ያስተላለፈው ብይን ነው። ለጋዜጠኞች መብት የሚታገለው አቀፉ ዓለምድርጅት (CPJ ) ፤ በጋዜጠኛ

default

እስክንድር ነጋና በሌሎች የነጻ ፕረስ ጋዜጠኞች ላይ ብርቱ የእሥራት ብይን ማሳለፉን አውግዟል።የ CPJ የአፍሪቃ አስተባባሪ ሙሐመድ ኬይታ፣ «ኢትዮጵያ ፤ በፀጥታ ይዞታ ላይ የሚመክሩ የአፍሪቃን ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በማስተናገድ ላይ ሳለች፤ መንግሥት ፀረ አሸባሪነት የሚሰኘውን ትግል ፤ ሽፋን በማድረግ ፣ ሰላማዊ የተቃውሞ ድምፅን ለማፈን ተጠቅሞበታል » ብለዋል።

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (HRW) የአፍሪቃ ጉዳዮች ዋና ተመራማሪ ቤን ሮውሌንስ፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ሐሳብን በነጻ መግለጽ ለሚቻልበት መብትና ለፕረስ ነጻነት የኅዘን ቀን ነው ሲሉ ተናግረዋል። የእርሳቸውን አስተያየት ከማቅረባችን በፊት፣ በቅድሚያ ፤ ስለብይኑ ፤ ከቅርብ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ምን ይላሉ? የአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትኅ ፓርቲ የከፍተኛ አመራር አባልና ፣ በሰላማዊ መንገድ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በፓርላማ ብቸኛ የህዝብ እንደራሴ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ፤ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባልተቤት ፤ ጋዜጠኛ ሠርክ-ዓለም ፋሲል ፤ የህግ ጠበቃ አቶ ደርበው ተመሥገንና ጋዜጠኛ መሥፍን ነጋሽ እንዲህ ብለዋል

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 13.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15Xc1
 • ቀን 13.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15Xc1