ስለማሊ የተወያየው ዓለም አቀፍ ጉባዔ | አፍሪቃ | DW | 05.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ስለማሊ የተወያየው ዓለም አቀፍ ጉባዔ

ማሊ ተጨማሪ ርዳታ እንዲሰጣት ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዛሬ በብራስልስ መዲና ቤልጅየም ባካሄደው ጉባዔ ላይ መከረ። የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ካትሪን አሽተን በመሩት ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ የፅንፈኛ

default

የማሊ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቲማን ኡቤር ኩሊባሊ

ሙሥሊም ቡድኖች ስጋት የደቀኑባት የማሊ ጊዚያዊ ሁኔታ ያሳሰባቸው የተመድ፡ የአፍሪቃ ህብረት፡ የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታት የኤኮኖሚ ማህበረሰብ፡ የዓለም ባንክ እና ሌሎች የብዙ ሀገራት ተወካዮች ተሳታፊዎች ሆነዋል። ጽንፈኛ ሙስሊሞችን ከሰሜን ማሊ ለማስለቀቅ አሁንም ጦርነቱ ቀጥሏል። ከጦርነቱ በተቃራኒ ባለፈው ጎርጎሪዮሳዊው 2012 ዓመት፣ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በመንግስት ግልበጣና በማሊ ለሁለት መከፈል ምክንያት አልተሳካም። ሀገሪቷ በአንድ በኩል ከጽንፈኛ ሙስሊሞች ጋር እየተዋጋች በሌላ በኩል በሐምሌ መጨረሻ ሊካሄድ ለታቀደው ምርጫ ዘመቻ ዝግጅት ላይ ነች።የመንግስት ግልበጣ፣ ጦርነት፣ ክፍፍል፤ ማሊያውያን እኚህን ወደኋላ ትተው ማለፍ ይፈልጋሉ። ማሊያውያን አሁን «ሽግግር» የሚለውን ቃል ደጋግመው ያነሱታል፤ ወደ ተሻለች ማሊ የመሸጋገርያ ጊዜ። ባዲ ሂማ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በዴንማርክና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው የማሊ ብሔራዊ ተቋም ኃላፊና በምዕራብ አፍሪቃ የሰብዓዊ መብቶችና የዲሞክራሲ ሂደት ባለሙያም ናቸው፣

«ምርጫን ማካሄድ፣ ሁሌም ከቀውስ መውጫ እውነተኛ መንገድ ተደርጎ ይታያል። ታማኝና ግልጽ ምርጫን ማካሄድ ብሔራዊ እርቅን የማውረድ አንዱ መንገድ ነው።»

ምርጫ ትኩስ ኃይል እና አዲስ ስሞች እንዲወጡ፤ አዲስ የፓርላማና የመንግስት አወቃቀርም እንዲፈጠር እድል ይሰጣል። በዚህ ምርጫ ከፖሊቲካው የተገለሉ የአናሳ ቡድን ተወካዮችን፣ ለዘብተኛ ሙስሊሞችና የቱዋሬግ አርብቶ አደሮችን እንዲሁም ሴቶችን ማጠቃለል ይቻላል።«ብሔራዊ ሸንጎው እየተከራከረበት ያለው አካሄድ፤ የሽግግር ጊዜ መንግስት ባለስልጣናት፣ በፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ውስጥ እጩ ተወዳዳሪዎች ሆነው አለመቅረባቸው ጥያቄ ሊያስነሳ እንደማይገባ ግልጽ ያደረገ ይመስላል።»

የሽግግር መንግስቱ ፕሬዝዳንት ትራውሬና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኪሶኮ የመሳሰሉ የኋላ ወንበር ላይ መቀመጥ አለባቸው። ከማሊ አንድነት ፓርቲ፣ ኢብራሂም ቡባጃር ኬይታ እና «ADEMA» የተሰኘው ጥምር ፓርቲ እጩ ሞዲቦ ሲዲቤ ወደ ፊት ማሊን የሚመሩ እጩዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ሆኖም አብዛኞቹ ፓርቲዎች እጮዎቻቸውን ወደ ምርጫ ዘመቻ መች እንደሚልኩ ቀነ ገደብ አላስቀመጡም።

እአአ ለሐምሌ 31 የታቀደው ይህ ምርጫ ብዙ ምኞት ያዘለ ቢሆንም ተፈጻሚነቱ አጠራጣሪ ነው። አሁንም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ድምጽ መስጠት ከሚችሉበት ከማሊ ውጭ ናቸው። ከስድስት ሚሊዮን የሚበልጡ ድምጽ መስጠት የሚችሉ ዜጎች እስካሁን አልተመዘገቡም። የገንዘብ እጦትም ሌላው ችግር ነው። የዛሬው የብራሰልስ የለጋሽ ሀገራት ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዖላንድ ለማሊያውያን ማንኛውንም እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፣«አሁን ይህን ሽግግር፣ ዲሞክራሲና ምርጫን በውጤታማነት መወጣት አለባችሁ። በሐምሌ ምርጫችውን አድርጉ። ለአፍሪቃና ለሌላውም ዓለም ማሊ አርአያ መሆኗን አሳዩ። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከናንተ ጋር ነው።»

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግን የሚከፍለው በከፊል ነው። ከወታደራዊ እርምጃው ሌላ ለማሊ ምጣኔ ሐብታዊና ፖሊቲካዊ እድገት የሚሰጡ እርዳታዎች ከፍ ሊሉ አይገባም። በመቶ ሚሊዮን ዩሮ የሚቆጠሩ የልማት እርዳታዎች ባለፈው ዓመት እንዳይንቀሳቀሱ ተደርገዋል። አሁን የሚያስፈልገው ይህን ገንዘብ ተገቢው ሥራ ላይ ማዋል ነው። ማሊ ውስጥ ለሚካሄደው ምርጫ ማዋሉ አንዱ ምሳሌ ነው።

ሽቴፋን ኤህለርት

ገመቹ በቀለ

ገበያው ንጉሤ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic