ሴቶች | በማ ድመጥ መማር | DW | 22.10.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

በማ ድመጥ መማር

ሴቶች

የላይቤርያ ፕሬዝደንት ሴት ናቸው። የጎርጎሮሳዉኑ 2004 የሰላም ኖቤል ተሸለሚ ም ኬንያዊት ወይዘሮ ናቸው...

default

መራራ ሕይወት

መራራ ሕይወት

የላይቤርያ ፕሬዝደንት ሴት ናቸው። የአውሮፓውያኑ የ2004 የሰላም ኖቤል የተሸለሚ ኬንያዊት ወይዘሮ ናቸው። ሁለቱም በሺዎች ለሚ ቆጠሩ አፍሪቃውያን ሴቶች በአርአያነታቸው ይጠ ቀሳሉ። በማዳመጥ መማር ትኩረት ስለተነፈጋቸው ሴቶች መብቶችና ችግሮች የሚ ቃኙ ተከታታይ የሬድዮ ዝግጅቶችን ያቀርባል።

በዛሬይቱ አፍሪቃ ብዙ ልጃገረዶች የሴትነት ሕይወት ምን እንደሚ መስል ገና ከሕፃንነታቸው ጀምረው ያውቁታል። ከእንቅልፍ ማልዶ መንቃት፣ ምግብ ማብሰል፣ ልብስ ማጠብና የመሳሰሉት የቀን-ተቀን ሕይወታቸው አካል ናቸው። ወንድሞቻቸው ትምህርት ቤት ሲሄዱ ቢመለከቱም የወንድሞቻቸውን እድል ማግኘት ግን ለበዙዎቹ የማይታሰብ ሆኖባቸዋል።

ሴቶችም መብት አላቸው

ሴቶችን ስለመብታቸው ግንዛቤ ማስጨበጥ ከበማዳመጥ መማር ዓላማዎች አንዱ ነው። ዝግጅቶቹ የተቀረፁት ሁለቱም ፆታዎች ሊከታተሉት በሚ ችሉበት መልኩ ነው። የአድማጮችን ቀልብ በመሳብ ሴቶች ያሏቸውና ሊያዳብሯቸው ስለሚ ገቡ እምቅ ችሎታዎች እንዲያውቁ ይደረጋል።

አቀራረብ

በማዳመጥ መማር የተለመደው ዓይነት የሬድዮ ዝግጅት አይደለም። በሴቶች ሕይወትና ችግሮቻቸው ዙሪያ የሚ ያጠ ነጥኑ አስደሳች፣ መሳጭ፣ እንዲሁም አዝናኝ ዝግጅቶች ለታዳሚዎቹ ያቀርባል።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት በስድስት ቋንቋዎች ይቀርባል። ቋንቋዎቹም አማርኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ፖርቱጋልኛ ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ወይም ዝግጅቶቹን ለማዳመጥ ከፈለጉ እባክዎን www.dw-world.de/learning-by-ear የተሰኘውን ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል።