«ሴቶች ሁሉ የላቀ የማሰብ ችሎታ አለን» ሥራ ፈጣሪዋ ቤተልሔም ታደሰ | ባህል | DW | 16.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

«ሴቶች ሁሉ የላቀ የማሰብ ችሎታ አለን» ሥራ ፈጣሪዋ ቤተልሔም ታደሰ

ስንቶቻችን ሴቶች እችላለሁ ብለን ለቆምንለትን አላማ ለምንወደዉ ነገር፤ ልባችን የፈቀደዉን ነገር እንሰራለን?። ስንቶቻችንስ ፈተናዎችን አልፈን ስኬት ማማላይ ደርሰናል አልያም ወድቀናል? እኛ ሴቶች የላቀ የሆነ የማሰብ ችሎታ አለን፤ የምትለን  የ 28 ዓመትዋ ወጣት ቤቴልሔም ታደሰ፤ በስሩ ስምንት እህት ድርጅቶችን ያካተተ ኩባንያ መስርታለች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 14:31

በሥራ ፈጠራ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክላ ለዉድድር ደቡብ አፍሪቃ ላይ በእጩነት ቀርባለች

ስንቶቻችን ሴቶች እችላለሁ ብለን ለቆምንለትን አላማ ለምንወደዉ ነገር፤ ልባችን የፈቀደዉን ነገር እንሰራለን?። ስንቻችንስ ፈተናዎችን አልፈን ስኬት ማማላይ ደርሰናል? እኛ ሴቶች የላቀ የሆነ የማሰብ ችሎታ አለን፤ የምትለን  የ 28 ዓመትዋ ወጣት ቤቴልሔም ታደሰ፤ በስሩ ስምንት እህት ድርጅቶችን ያካተተዉን ኢትዮ ኤርስ ንግድና ኢንቨስትመንት ድርጅት አቋቁማ ለሦስት ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድልን ፈጥራለች።

በቅርቡ በኢትዮጵያ  ነጋዴ ሴቶች ማኅበር አማካኝነት በደቡብ አፍሪቃ በየዓመቱ በሚካሄደው የአፍሪቃ ሴቶች የሥራ ፈጠራ ማለትም ኢኖቬሽን እና ኢንተርፕርነርሺፕ ሽልማት ዉድድር ላይ በወጣት ስራ ፈጣሪዎች  ዘርፍ ከበርካታ ኢትዮጵያዉያት መካከል ተመርጣ በአፍሪቃ አቀፉ መድረክ ላይ ለመወዳደር በዕጩነት ቀርባለች። ለዚህ እድል  በመብቃትዋ ደስተኛ እንደሆነች የምትገልፀዉ ቤተልሔም ታደሰ፤ አሁን ብቻ ሳይሆን በተማሪነት እድሜዋም ጠንካራ ነበረች፣ ትምህርቷን ያጠናቀቀችዉም የወርቅ ሜዳልያን በማግኘት እንደሆነ ትናገራለች። 

ከአሜሪካ ሰብዓዊ ተራድኦ ድርጅት (USAID)ጋር በመተባበር ደቡብ አፍሪቃ ላይ በየዓመቱ በሚካሄደው የአፍሪቃ ሴቶች የሥራ ፈጠራ ማለትም ኢኖቬሽን እና ኢንተርፕርነርሺፕ ሽልማት ዉድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክላ በእጩነት

የቀረበችዉ ቤተልሔም ታደሰ፤ ያቋቋመችዉ ድርጅት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያም ሆነ ብሎም በዓለማችን የብዙ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘዉን የኮሮና ተኋዋሲ ለመግታት የፀረ-ተህዋሲ ኬሚካል ርጭት እያከናወነ በመሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድሐኒትና የጤና ክብካቤ  አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን እና ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀትን አግኝቶአል። ድርጅቱ ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ ፀረ-ተዋህሲ መድሐኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የርጭት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝም  ወጣትዋ ሥራ ፈጣሪ ነግራናለች።  

በኢትዮጵያ  ነጋዴ ሴቶች ማኅበር ይፋ እንዳደረገዉ 48 የአፍሪቃ ሃገራት የሚሳተፉበት የሥራ ፈጣሪ ሴቶች ዉድድር ላይ በእጩነት የቀረበትዉ ቤተልሔም ታደሰ፤ ድርጅቶችን አቋቁሞ መስራትን እንዴት አሰበችዉ እንዴት ተሳካልትስ ?  
በደቡብ አፍሪቃ የቀረበችበት ዉድድር አሸናፊስ መቼ ነዉ የሚገለፀዉ? የኢትዮ ኤርስ ንግድና ኢንቨስትመንት ኮባንያ መስራችና ተጠሪ ወጣት ቤተልሔም ታደሰ፤ ለኢትዮጵያዉያን ሴቶች ያስተላለፈችዉ መልዕክትም አላት። ዝግጅቱን ይከታተሉ።  

ዶቼ ቬለ ወጣት ቤተልሔም ታደሰ ኢትዮጵያን  ወክላ በእጩነት በቀረበችበት መድረክ አሸናፊ ሆና አገርዋን እንድታስጠራ ለብዙዎችም አርዓያ እንድትሆን ይመኛል።  ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። 

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ 

Audios and videos on the topic