ሴራሊዮን በኢቦላ ተሐዋሲ ፍራቻ መዲናዋን በከፊል ዘጋች | አፍሪቃ | DW | 14.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ሴራሊዮን በኢቦላ ተሐዋሲ ፍራቻ መዲናዋን በከፊል ዘጋች

ሴራሊዮን መዲና ፍሪታውን ውስጥ 6 ግለሰቦች ላይ እንደ አዲስ የኢቦላ ተሐዋሲ ምልክት በመታየቱ በመዲናዋ የሚገኙ 700 ቤቶች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች መግባት መውጣት መከልከላቸው ተዘገበ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢቦላ ተሐዋሲን በተመለከተ በሀገሪቱ የተመደበ አንድ የሒሳብ አጣሪ ወይም ኦዲተር የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ለኢቦላ ድንገተኛ አደጋ በሚል ከተሰበሰበው 17 ሚሊዮን ዩሮ ውስጥ አንድ ሦስተኛውን ያህል ያለምንም ተጠያቂነት አባክነዋል ሲል አጋልጧል። ባከነ የተባለው ገንዘብ በአብዛኛው ከግብር እና በርዳታ ከተገኙ ድጋፎች ጋር ተያያዥነት ያለው መሆኑም ተጠቅሷል። ይህ የባከነ ገንዘብ ግን ኢቦላን ለመከላከል በሚል ለሴራሊዮን በተመድ ከተመደበው አለያም ከዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተሰበሰበውን ገንዘብ የሚመለከት አለመሆኑም ተነግሯል። ለኢቦላ መከላከል ተሰብስቦ እንደባከነ የተጠቀሰው በሚሊዮን የሚቆጠር ዩሮ በመንግሥት በኩል ለጤና ባለሙያዎች የአገልግሎት ክፍያ፣ የመድሐኒት እና የህክምና ቁሳቁስ መግዢያ ውሏል መባሉም ተገልጧል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ