«ሳይነስ» በትክክል ምንድነዉ? | ጤና እና አካባቢ | DW | 04.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

«ሳይነስ» በትክክል ምንድነዉ?

እዚህ ጀርመን በክረምቱ የሚታዩት ተስፋ የሌላቸዉ የሚመስሉት ጭራሮዋቸዉ የተንጨፈረረ ዛፎች፤ ያ ምህረት የለሽ የበረዶ እና ቅዝቃዜ ወራት ገሸሽ ሲል፤ ከየት መጣ ሳይባል አረንጓዴ ቅጠላቸዉ ማቆጥቆጥ፤ አበባቸዉ አድሮ መፍካት ይጀምራል። ይህን ወቅት ታዲያ ሁሉም እኩል አያጣጥመዉም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:17

የማያቋርጠዉ ማስነጠስ አፍንጫን ያቀላል፤

ከቅዝቃዜዉ ለመላቀቅ እንዳልጓጓ፤ የአቦቹ ፍካት፤ የአንዳንድ ተክሎች ቅጠል ብናኝ ጤና የሚነሳዉ ቁጥሩ ቀላል አይደለም። አንዳንዶች አበቦች ሲፈኩ እነሱ አይደሰቱም። ሌሎች አቧራ በቀላሉ ይረብሻቸዋል። የቆሻሻ ብቻ ሳይሆን የመልካም ሽቱ መዓዛም ማስነጠስ አከታትሎባቸዉ አፍንጫቸዉ ፈሳሽ ያመነጫል፤ ዓይናቸዉ እንባ ያዘንባል። እናም ምነዉ ሲባሉ? ሳይነስ አለብኝ ይላሉ። በልማድም ሳይነስ አለብኝ፤ አለበት ወይም አለባት ይባላል። ለመሆኑ ሳይነስ የምንለዉ የጤና ችግር ምንድነዉ? የአንድ የዝግጅታችን ተከታታይ ጥያቄ ነዉ ዛሬ ይህን እንድንቃኝ የመራን። ህክምናዉ ስለዚህ የጤና ችግር ምን ይላል? ከድምጽ ዘገባዉ ሙሉ ቅንብሩን ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic