ሳዑዲ የፈታታቸው እሥረኞች ወደ ሐገራቸው ገቡ | ኢትዮጵያ | DW | 21.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሳዑዲ የፈታታቸው እሥረኞች ወደ ሐገራቸው ገቡ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 1085 ከእስር የተለቀቁ ኢትዮጵያውያን  ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:08

ሳዑዲ የፈታታቸው ኢትዮጵያውያን እስረኞች ሀገራቸው ገቡ

ሳዑዲ አረብያ በምሕረት ከእስር የለቀቀቻቸው ኢትዮጵያውያን እሥረኞች ከትናንት በስተያ አንስቶ ወደ ሀገራቸው ገብተዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 1085 ከእስር የተለቀቁ ኢትዮጵያውያን  ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል። እስረኞቹ የተፈቱት በቅርቡ ሳውዲ አረብያን የጎበኙት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያውያኑ እንዲፈቱ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት መሆኑን መንግሥት አስታውቋል። ከሳዑዲ እስር ቤቶች ስለተፈቱ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የጅዳውን ወኪላችንን ነብዩ ሲራክን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ነብዩ ሲራክ 
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic