ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን | ኢትዮጵያ | DW | 12.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን

አሁንም እዚያዉ ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተለያየ ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸዉን እያስታወቁም ነዉ።በስልክ ያነጋገርናቸዉ ኢትዮጵያዉያን እንደሚሉት ወደ ሐገራቸዉ ለመግባት ቢፈልጉም ከሳዑዲ አረቢያ ፀጥታ አስከባሪዎች የሚደርስባቸዉን ድብደባና በደል ፍራቻ በየቤታቸዉ ለመሸሸግ ተገድደዋል።

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ ሕገ-ወጥ የዉጪ ሐገር ነዋሪዎችን ከሐገሩ ማበረሩን ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹን ወደ ሐገር ለመመለስ መዘጋጀቱን ቢያስታዉቅም ስደተኞቹ እንደሚሉት እስካሁን ሁነኛ እርምጃ አልጀመረም።አሁንም እዚያዉ ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተለያየ ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸዉን እያስታወቁም ነዉ።በስልክ ያነጋገርናቸዉ ኢትዮጵያዉያን እንደሚሉት ወደ ሐገራቸዉ ለመግባት ቢፈልጉም ከሳዑዲ አረቢያ ፀጥታ አስከባሪዎች የሚደርስባቸዉን ድብደባና በደል ፍራቻ በየቤታቸዉ ለመሸሸግ ተገድደዋል።በየቤቱ የተሸሸጉት ደግሞ የምግብና የዉሐ እጥረት እንዳጋጠማቸዉ እየተናገሩ ነዉ።ጅዓፈር ዓሊ አስተያየቶችን አሰባስቧል።

ጅአፈር ዓሊ

አርያም

Audios and videos on the topic