ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢትዮጵያዉያንን ማጋዟን ቀጥላለች | ዓለም | DW | 18.08.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢትዮጵያዉያንን ማጋዟን ቀጥላለች

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት «ሕገ-ወጥ» በማለት በየማቆያ ማዕከሉ (እስር ቤቶች) የያዛቸዉን ተጨማሪ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ወደ ሐገራቸዉ መላክ ጀመረ። የኢትዮጵያና የሳዑዲ አረቢያ መንግስታት ባደረጉት ስምምነት መሰረት እስካሁን በተለያዩ የሳዑዲ አረቢያ ማቆያ ጣቢያዎች የታሰሩ ኢትዮጵያዉያን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሐገራቸዉ እንደሚላኩ ተገልጧል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:04

«ኢትዮጵያዉያን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሐገራቸዉ ይላካሉ»

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት «ሕገ-ወጥ» በማለት በየማቆያ ማዕከሉ (እስር ቤቶች) የያዛቸዉን ተጨማሪ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ወደ ሐገራቸዉ መላክ ጀመረ። በጂዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ምክትል ኃላፊ ነብዩ ተድላ ዛሬ ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት የኢትዮጵያና የሳዑዲ አረቢያ መንግስታት ባደረጉት ስምምነት መሰረት እስካሁን በተለያዩ የሳዑዲ አረቢያ ማቆያ ጣቢያዎች የታሰሩ ኢትዮጵያዉያን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሐገራቸዉ ይላካሉ። በዕዱ መሠረት በየሳምቱ በሶስቴ በረራ 1ሺሕ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሐገራቸዉ ይሔዳሉ። በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆስላ ጽሕፈት ቤቶች ስደተኞቹ ኢትዮጵያዉና መሆናቸዉን በመለየት፣ ሰነድ በማዘጋጀት፣የፍርድ ቤት ክስ ያለባቸዉን ጉዳያቸዉን በመጨረሽ፣ መብታቸዉ መጠበቁን በመከታተል በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በመስራት የስደተኞቹን የመልስ ጉዞ ያመቻቻሉ። ነጋሽ መሐመድ አቶ ነብዩ ተድላን በስልክ አነጋግሯቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic