ሳውዲ አረቢያ ወህኒ የተረሱ ኢትዮጵያውያን | ኢትዮጵያ | DW | 21.05.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሳውዲ አረቢያ ወህኒ የተረሱ ኢትዮጵያውያን

ኢትዮጵያውያኑ የሃገራቸው የኤምባሲና የቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ጉዳያቸውን ስለማይከታተሉላቸው በእስር ቤት አለአግባብ እየተንገላቱ መሆናቸውን ተናገረዋል ፡፡

ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በሪያድና በጀዳ ከተሞች ተፈርዶባቸው የእስር ቅጣታቸውን ጨርሰው አሁንም የታሰሩና ተጠርጥረው ከታሰሩ በኋላ ሳይፈረድባቸው በወህኒ የሚገኙኢትዮጵያውያን ምሬታቸውን ለዶቼቬለ አስታወቁ ። ኢትዮጵያውያኑ የሃገራቸው የኤምባሲና የቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ጉዳያቸውን ስለማይከታተሉላቸው በእስር ቤት አለአግባብ እየተንገላቱ መሆናቸውን ተናገረዋል ፡፡ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች በበኩላቸው የእስረኞቹ ጉዳይ እንዲጣራ ለሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ደብዳቤ መፃፋቸውንና ሃላፊዎችንም ለማነጋገር ቀጠሮ መያዛቸውን አስታውቀዋል ነብዩ ሲራክ ከጅዳ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ነብዩ ሲራክ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ,

Audios and videos on the topic