ሳዉዲ የሚሰቃዩ ዜጎች ጉዳይ ያነሳዉ ተቃዉሞ | ኢትዮጵያ | DW | 14.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሳዉዲ የሚሰቃዩ ዜጎች ጉዳይ ያነሳዉ ተቃዉሞ

ሳዉድ አረቢያ በሚገኙ ዜጎች ላይ የሚፈፀመዉን ጥቃት በመቃወም ከጀርመን የተለያዩ ከተሞች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዉያን ፍራንክ ፈርት ላይ ዛሬ ሰልፍ አካሄዱ።

በጀርመን የሳዉዲ ቆንስላ በሚገኝበት ስፍራ በሃዘንና ቁጣ መሰባሰባቸዉን የገለፁት ሰልፈኞች ሳዉድ አረቢያ ኢትዮጵያዊ እህቶቻችንን መግደልና መድፈር፤ ወንድሞቻችን ማሰቃየትና መግደል አቁሚ የሚል መፈክራቸዉን ሲያሰሙ አርፍደዋል። ሰልፉ በጀርመን ሰዓት ከቀትር በፊት የጀመረ ሲሆን ከቆንስላዉ የሳዉዲ ተወካዮች ወጥተዉ ደብዳቤ ካልተቀበሏቸዉ አካባቢዉን እንደማይለቁ የገለፁት እነዚህ ወገኖች በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ሊደረግ የማይገባዉ የጭካኔ ተግባር ያሉትን ድርጊትም እንዴት ያለ ምግባርና እንዴት ያለ ሰብዓዊነት ነዉ ሲሉም ኮንነዋል። ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዷ የሆኑት ወይዘሮ አሳየሽ ታምሩ ሮይሽልን ስለተካሄደዉ ሰልፍ በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ፤

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic