1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳምንታዊዉ ስፖርት

ሰኞ፣ ግንቦት 13 2010

ትላንት በላቲቪያ በተካሂደው የሪጋ ማራቶን በወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌት አያና ሳዳት አንደኛ በመሆን አዲስ የርቀቱን ሰአት አስመዝግቧል።  ከ 78 ሃገራት የመጡ ታዋቂ አትሌቶችን ጨምሮ 37,600 አትሌቶች በተካፈሉበት የሪጋ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት አያና ሳዳት አዲስ የርቀቱን ሰአት ሲያስመዘገግብ እማኝ ሆነዋል።

https://p.dw.com/p/2y4Se
DFB-Pokal Finale 2017/2018 FC Bayern München - Eintracht Frankfurt: Jubel
ምስል Reuters/K. Pfaffenbach

የሪጋ እና ማንችስተር ማራቶን ድሎች

 አያና 2 ሰአት ከ11 ደቂቃ ከ00 ሰከንድ በመግባት ነው ያሸነፈው። ከውድድሩ አስቀድሞ ያሽንፋል የሚል እምንት የተጣለበት ኪንያዊው አትሌት ኪፕሮኖ ቱ 2 ሰአት 11 ደቂቃ ከ 13 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ሆንዋል። ሌላው አትሌት ሙናዮኪ 2 ሰአት ከ13ደቂቃ 10 ሰከንድ  በመግባት ሶስተኛ ሆኖ ውድድሩን ፈጽሟል።

የሴቶች ማራቶን ውድድር እንደተጠበቀው ሁሉ በኬንያዊትዋ አትሌት  ጂዮርጂና ጂፕኪሩኢ  ሮኒ አሸናፊነት ተጠናቋል። አስቀድሞ ውድድሩን እንደምታሸንፍ ግምት የተሰጣት ሮኒ  2 ሰአት 28  ደቂቃ ከ 02  ሰከንድ የገባች ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊትዋ አትሌት ትዕግስት ተሾመ  ደግሞ 2 ሰአት 32 ደቂቃ ከ 46  ሰከንድ  በመግባት ሁለተኛ ሆናለች። ሌላዋ ኬንያዊት አትሌት ፓሊን ኑጂሪ 2 ሰአት 34 ደቂቃ ከ 41 ሰከንድ በመግባት የነሐስ ሚዳልያውን ወስዳለች።

በብሪታንያ ማንችስተር ትላንት በተካሂደው የግሪት ማንችስተር የ10ሼህ ሜትር ውድድር አትሊት ሞ ፋራ እና አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አሸናፊ ሆነዋል። አትሌት ጥሩነሽ ፈጣን ባልነበረው ውድድር ያለምንም ችግር 31  ደቂቃ ከ08  ስትገባ፤ በማንችስተር በሚደረገው በዚህ ውድድር በተከታታይ  3 ኛ ግዜ በአጠቃላይ ደግሞ ለ 5 ኛ ግዜ ማሸነፏ ነው። በወንዶች አትሌት ሞ ፋራ 28 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ በመግባት አንደኛ ሆኖ ሲጨርስ፤ ኤትዮጵያዊው አትሌት  ደጀኔ ገዝሙ አምስተኛ ሆኖ ጨርስዋል፤ የገባበትም ሰአት 30 ደቂቃ ነው።
ባለፈው ዓመት በአሸባሪዋች ጥቃት ሕይወታቸው ላለፈው 22 ሰዎች የአንድ ደቂቃ ሕሊና ጸሎት በማድረግ የተጀመረው  ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች የተካፈሉበት ይህ ማንችስተር ውድድ በታላቅዋ ብሪታንያ በርካቶችን በማሳተፍ የሚታወቅ ሦስተኛ የውድድር መድረክ ነው።

Römer Pokalfeier Eintracht Frankfurt DFB-Pokal
ምስል picture-alliance/dpa/B. Roessler


እግር ኳስ
137ኛው የእንግሊዝ ማኅበረሰብ ዋንጫ ጨዋታ ኤደን ሀዛርድ በመጀመሪያው ግማሽ  በፍፁም ቅጣት ምት በማንችስተር ዩናይትድ ላይ ባስቆጠረው ጎል ቸልሲን የዋንጫው ባለቤት አድርጎታል። አሰልጣኝ አንቶንዮ ኮንቲ ቡድናቸው የኤፍ ኤን ዋንጫ ቢያነሳም ሥራቸውን ግን ከማጣት አላዳናቸውም።


የጀርመን የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ
ፍራንክፈርት የቡንደስ ሊጋን የዋንጫ ባለቤት ባየር ሙንሽንን  3 ለ 1 በማሸነፍ ዋንጫውን ወስዷል።  በቡንደስ ሊጋው ከ መሪው ባየር ሙንሽን በ 35 ነጥብ ዝቅ ብሎ  8ኛ ሆኖ የጭረሰው ፍራክፈርት፤ ከ1988 እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር  በኋላ የመጀ መሪያ ዋንጫቸው ነው።  ባየር ሙንሽኖች ዘንድሮ ሁለቱንም የ አገሪቱን ዋንጫ የማግኘት ሕልማቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

በስፔን ፕርሚየራ ሊጋ የ መጭረሻ ሳምንት ጨዋታ ትላንት አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ኤባር 2 ለ 2 ተለያይቶ ነጥብ ተጋርቶ ሲወጣ ፈርናንዶ ቶሪዝ ነበር። ሁለቱንም ጎሎች ከመረብ ያገናኛው ሉካስ ህርናንዲስ  በ 63 ኛ ው ደቂቃ በሁለት ቢጫ ከሜዳ በቀይ ከወጣ በኋላ በጎዶሎ ልጅ የተጫወቱት አትሌቲኮ ማድሪዶች በ 7 ደቂቅ በተቆጠረባቸው ጎል አቻ በመውጣት ላሊጋውን በ 79 ነጥብ ሁለተኛ ሆነው ጨርሰዋል። የተገባደደውን የስፔን ላሊጋ በ መሪነት ያጠናነቀው ባርሴሎና፤ ሪያል ሶሲዳዲን 1 ለ 0 አሽንፏል። 22 ድሎችን ለ 16ዓመት ከቡድኑ ጋር በመሆን ላገኛው የ 34 አመት የመሀል ተጫዋች  አንድሪያስ አኒስታ ደማቅ የስንብት ዝግጅትም አድርገዋል ። በተመሳሳይ ቫሊንሲያ ዲፖርቲዐኦ ላካሮኛን 2 ለ 1 ሲረታ አትሊቲኮ ቢልባኦ በ ኤስፓኞል 1 ለ 0 ተረትዋል።
የስፔን ላሊጋ ሲጠናቀቅ ባርሴሎና በ 93 ነጥብ ላሊጋውን ቀዳሚ ሆኖ ሲጭርስ አትሊቲኮ ማድሪድ በ 79 ነጥብ ሁለተኛ ሪያል ማድሪድ በ 76 ነጥብ ሶስተኛ ዐኣሊንሲይ በ 73 ናጥብ 4 በመሆን አጠናቋል። ዲፖርቲቮ ላካሮኛ ላስፓልማስ እና ማላጋ ላሊጋውን የተሰናበቱ ቡድኖች ናቸው። በጉጉት የሚጥበቀው የራሺያው የ አለም ዋንጯ ሊጀመር 24 ቀናት  ወይም 5 ሳምንት ብቻ  ይቀረዋል።

TOPSHOT-TENNIS-ITALY-ATP
ምስል AFP/Getty Images


ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ