ሲጋራ ማጨስን የሚገድበው ህግና ወጣቱ | ባህል | DW | 31.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ሲጋራ ማጨስን የሚገድበው ህግና ወጣቱ

ወጣቱ ሲጋራ ማጨስ በሚያዘወትርበት በአሁኑ ወቅት ይሄ ህግ መፍትሄ ይሆን ይሆን? በዛሬው የወጣቶች ዓለም እንመለከተዋለን።

በዮናይትድ ስቴትስ በሳምባ ካንሰር የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዓመት ወደ ዓመት እየቀነሰ እንደመጣ አዲስ የወጣ መዘርዝር ያስረዳል። እንደጥናቱ ለዚህም ምክንያቱ ሲጋራ ማጨስን ለማስቆም የሚደረጉ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ናቸው። ህዝብ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ማጨስ በበርካታ ሀገራት ተከልክሏል። በትምባሆ ላይም ከፍተኛ ግብር ተጥሏል። ይህም በኢትዮጵያ ተግባራዊ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አውጇል።

ህዝብ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ትንባሆ ማጨስ የሚከለከሉበት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። አጫስ ያልሆኑ ሰዎችን ደህንነት መጠበቅ ፣ ወጣቶች በቀላሉ ለማጨስ እንዳይነሳሱ ማድረግ እና በተለኮሰው ሲጋራ አማካኝነት ቃጠሎ እንዳይነሳ ማድረግ ከምክንያቶቹ ጥቂቶቹ ናቸው። በሌሎች ሀገራት በተግባር ላይ የዋለው ትንባሆ የማይጨስባቸው አካባቢዎችን የደነገገ ህግ በኢትዮጵያም ተግባራዊ ሆኗል። በኢትዮጵያ የምግብ ፣መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን፤ ምክትል ዋና ዳሬክተር ፤ አቶ መንግሥትዓብ ወልደአረጋይ በደንቡ ላይ የተቀመጠው ትምባሆ የማይጨስባቸው አካባቢዎች የትኞቹ እንደሆኑ አብራርተውልናል።

ናትናኤል በአዲስ አበባ የሚኖር ወጣት ነው። ሲጋራ ማጨስ የጀመረው ገና ታዳጊ ወጣት ሳለ ነው ። እንደዛሬው ይፋ ሳይሆን በፊት ከቤተሰቦቹ ተሸሽጎ ነበር የሚያጨሰው፤ ናትናኤል ምንም እንኳን አጫሽ ቢሆን እና ድንጋጌው በመጀመሪያ ደረጃ ቢመለከተውም አዲሱ ህግ ኢትዮጵያም ተግባራዊ መሆኑን ይደግፋል።

በዚህ በጀርመን ከ4 ሰዎች አንዱ አጫስ እንደሆነ ይነገራል። ቢሆንም በ2002 የተሸጠው ሲጋራ ቁጥር እኢአ 2012 ጋ ሲነፃፀር። ከ 145 ቢሊዮን ወደ 82 ቢሊዮን ዝቅ ብሏል። ዳግማር ቲስ በጀርመን ሀገር የምትኖር ወጣት ናት። በመላው ጀርመን እኢአ ከየካቲት 2011 ዓ ም ጀምሮ ህዝብ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ማጨስ ሲከለከል ውሳኔውን በደስታ ተቀብላዋለች። በኢትዮጵያ በስራ ላይ እንዲውል የታቀደውም አዲስ ህግም የወጣት አጫሹን ቁጥር ሊቀንስ ይችላል ብላ ታምናለች።

ትንባሆ የማይጨስባቸው አካባቢዎችን የደነገገውን ህግ መነሻ ያደረገውን የዛሬውን የወጣቶች ዓለም ሙሉ ዝግጅት ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች