ሱዳን፤ የኤርትራና ኢትዮጵያ ስደተኞች | አፍሪቃ | DW | 01.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ሱዳን፤ የኤርትራና ኢትዮጵያ ስደተኞች

የሱዳን መንግሥት በቅርቡ ከ400 የሚበልጡ ኤርትራዉያን ጥገኝነት ፈላጊዎችን ወደ ሀገራቸዉ መመለሱን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዉማን ራይትስ ዎች አወገዘ። ሌሎች የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR እንዳያገኛቸዉ ተደርጓል ያላቸዉን የታሠሩ 64 ኢትዮጵያዉያንም ዕጣ ይህ ሊሆን እንደሚችል ድርጅቱ አመልክቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:47
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:47 ደቂቃ

የኤርትራና ኢትዮጵያ ተሰዳጆች ዕጣ

ዓለም አቀፍ ሕግ ጥገኝነት ፈላጊዎች የተገን መጠየቂያ ማመልከቻቸውን ሳያቀርቡ እና ጉዳያቸዉ ሳይታይ በግዳጅ ከገቡበት ሀገር እንዳይባረሩ እንደሚከለክል ሂዉማን ራይትስ ዎች ያመለክታል። የሱዳንመንግሥትወደግዛቱየገቡ442 ኤርትራዉያን ይህን ዕድል ሳያገኙ ሰሞኑን ወደሀገራቸዉ እንደመለሳቸዉ ነዉ ሂዉማን ራይትስ ዎች ይፋ ያደረገዉ። ከመካከላቸዉ ስድስቱ በተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR የተመዘገቡ እንደነበሩም ጠቅሷል። ሂዉማን ራይትስ ዎች ተመሳሳይ ዕጣ ሊደርስባቸዉ እንደሚችል የጠቆመዉን 64 ኢትዮጵያዉያን ተሰዳጆች ደግሞ UNHCR እንዳያገኛቸዉ የሱዳን መንግሥት በማገድ ማሠሩንም አመልክቷል። ለምን ይሆን የሱዳን መንግሥት ይህን ያደረገዉ? የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌቭኮቭ ለሱዳን ይህ የመጀመሪያ አይደለም ይላሉ፤

«ሱዳን መንግሥት ኤርትራዉያን እና ኢትዮጵያዉያንን ወደየሀገራቸዉ ሲመልስ ይህ የመጀመሪያ አይደለም። ሆንም ግን የሚያሰጋዉ የተለመደዉ አካሄድ አካል መሆኑ ነዉ። ምክንያቱም በግንቦት ወር አንድ ብቻ ሳይሆን ኤርትራዉያንን ወደሀገር የመመለስ በርካታ አጋጣሚዎችን መዝግበናል። እናም በሱዳን መንግሥት እና ወደአዉሮፓ የሚደረገዉን ስደተት የመቀነስ ሃሳብ ባሳሰባቸዉ የአዉሮጳ ሃገራት መካከል በቅርቡ ከተደረገዉ አዲስ መርሃግብ እና ትብብሮች ጋር ግንኙነት ሳይኖረዉ አይቀርም የሚል ስጋት አለን።»

ወደአዉሮጳ የሚገባዉ የስደተኛ ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ስጋት የፈጠረባቸዉ የአዉሮጳ ሃገራት ከአፍሪቃውያን መሪዎች ጋር በተለያዩጊዜያትበዚህጉዳይመነጋገራቸዉይታወሳል።ባለፈዉ ኅዳር ወር ማልታ ላይ በተካሄደዉ የቫሌታዉ ጉባኤ ይህን ዋና ጉዳይ አድርገዉ ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር የተነጋገሩት የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች እስከ ሁለት ቢሊየን ዩሮ ለመስጠት መዘጋጀታቸዉን ይፋ አድርገዋል። እንዲያም ሆኖ በምን መልኩ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል የተነገረ ዝርዝር መረጃ የለም።ሌስሊ ሌቭኮቭ የሱዳንን ርምጃ በቀጥታ ከዚህ ስምምነት ጋር ለማገናኘት ያዳግታል ነዉ የሚሉት።

«እንዳልኩት ኤርትራዉያንን ሱዳን ወደሀገራቸዉ ስትመልስ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፤ እናም ግልፅ የሆነ ግንኙነት ከዚህ ጉዳይ ጋር አለ ብሎ ለማሰብ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ምክንያቱም በ2014 እና በ2011ንድም በተመሳሳይ ሁኔታ በማሰር፤ ወይም ከጥገኝነት ሰጪ ተቋማት ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ ም የሱዳን ባለስልጣናት ኤርትራዉያንን ወደ ሀገራቸዉ መመለሳቸዉን እናዉቃለን። እናም የመጀመሪያ አይደለም። እንዲያም ሆኖ በሱዳን እና በአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት መካከል ይህ ትብብርና መርሃግብር በመኖሩ እንዲህ ያለዉን ርምጃ በተደጋጋሚ ልናይ እንችላለን የሚል ሥጋት ግን አለ።»

Human Rights Watch Logo

ከሶስት ሳምንታት በፊት የሱዳን ባለስልጣናት ወደ ሊቢያ ሊሻገሩ ያለሙ 377 ስደተኞችን ዶንጎላ በተባለች የድንበር ከተማ ይዘዉ ማሠራቸዉን UNHCR ያመለክታል። ከእነሱ መካከል 313ቱ ኤርትራዉያን ናቸዉ። ስድስቱ ደግሞ በጥገኝነት ፈላጊነት እዚያዉ ሱዳን ዉስጥ ተመዝግበዋል። ቀሪዎቹ ኢትዮጵያዉያን ሲሆኑ ሁሉም በሕገወጥ መንገድ ወደሱዳን በመግባት ተከሰዋል። ኤርትራዉያኑ ወደ ሀገራቸዉ ተገደዉ ሲላኩ ኢትዮጵያዉኑ ታሥረዋል። ወደኤርትራ የተመለሱት ስደተኞች ዕጣም ሆነ የታሠሩት ምን ሊሆን ይችላል። ሌቭኮቭ እንዲህ ይላሉ፤

«ኤርትራን በሚመለከት እኛም ሆንን የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽኑ የረዥም ጊዜ ስጋት አለን። ወደኤርትራ የተመለሱት እሥራት፤ ስቃይ እና እንግልት ሊገጥማቸዉ ይችላል። ስለዚህም ኤርትራዉያንን ወደሀገራቸዉ መመለሱ ከፍተኛ ስጋት አለዉ። ባለፉት ጊዜያት የኤርትራዉያን የጥገኝነት ጥያቄያቸዉ አዎንታዊ ምላሽ ከሚያገኝባቸዉ ምክንያቶች አንዱም ይህ ነዉ። ኢትዮጵያዉያኑን ስንመለከት የተደባለቀ የስደት ሁኔታ ነዉ ያለዉ። የተሻለ የኤኮኖሚ ዕድል ለማግኘት የሚሰደዱ ኢትዮጵያዉያን አሉ፤ የሚደርስባቸዉን ክስ በመፍራት የሚሰደዱም አሉ። እርግጥ ኢትዮጵያዉያ ዉስጥ የሚፈጸም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የሚሸሹም አሉ። እናም ከተመለሱ መጥፎ የሆነ ይዞታ ይጠብቃቸዋል ብለን እንሰጋለን።»

ለዚህም ነዉ ይላሉ ሌቭኮቭ UNHCR የታሠሩትን ኢትዮጵዉያን ስደተኞች በማግኘት ለስደት ያበቃቸዉን ምክንያት ማጣራቱ በጣም የሚያስፈልገዉ። HRW የከዚህ በፊት ወደኤርትራ የተመለሱ ጥገኝነት ፈላጊዎች የደረሰባቸዉን እንግልት ቢጠቅሱም ሰሞኑን ተመለሱ ያላቸዉ ከ400 የሚበልጡት ተሰዳጆች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ድርጅታቸዉ የደረሰዉ መረጃ እንደሌለም ሳይገልጹ አላለፉም። ሱዳን የምታካሂደዉ ስደተኞችን ወደየሀገራቸዉ የመመለስ ርምጃ በምን መልኩ ሊስተካከል ይችል ይሆን?

«ምን እየተደረገነዉ ለሚለዉ የሚሰጠዉ ትኩረት ጠቃሚ ነዉ ብዬ አስባለሁ። በሱዳንና በአዉሮጳ ወይም በሌሎች ሃገራት መካከል ዉይይት የተካሄደበት መርሃግብር ምናልባት ጥሩ ሊሆን ይችላል። እስካሁን ስለመርሃግብሩ ዝርዝር ምንም አናዉቅም። ሆኖም ግን እጅግ በጣም በጥንቃቄ ሊከናወን ይገባል። እናም እንዲህ ያለዉ ትብብር ለሱዳንም ሆነ ለሌሎች፤ ሰዎች ጥገኝነት የመጠየቂያ ምን ዕድል ሳያገኙ እንደፈለጉ ወደየሀገራቸዉ መመለስ እንዲሚችሉ የሚያደርግ መልዕክት ማስተላለፍ የለበትም።»

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic